የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በተስፋችሁ ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ጥቅምት
    • 2 የሰይጣን ዓለም ክፍል የሆኑ ሰዎችም ተስፋ የሚያደርጓቸው ነገሮች አሉ፤ ሆኖም ተስፋቸው መፈጸም መቻሉን ይጠራጠሩ ይሆናል። ለምሳሌ ያህል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቁማርተኞች ሎተሪ እንደሚያሸንፉ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ይሁንና ማሸነፋቸውን እርግጠኞች መሆን አይችሉም። በሌላ በኩል ግን እውነተኛ እምነት ሲባል ለክርስቲያኖች የተሰጠውን ተስፋ “በእርግጠኝነት መጠበቅ” ማለት ነው። (ዕብ. 11:1) ይሁንና በተስፋህ ላይ ያለህን እምነት ይበልጥ ማጠናከር የምትችለው እንዴት ነው? ደግሞስ ተስፋ በምታደርጋቸው ነገሮች ላይ ጠንካራ እምነት ማዳበርህ ምን ጥቅሞች ያስገኛል?

      3. የክርስቲያኖች እምነት በምን ላይ የተመሠረተ ነው?

      3 እምነት፣ ኃጢአተኛ የሆኑ የሰው ልጆች ሲወለዱ ጀምሮ የሚኖራቸው ባሕርይ አይደለም፤ በራሱ ሊዳብርም አይችልም። እምነት ማዳበር ከፈለግን የአምላክ መንፈስ ልባችንን እንዲመራው መፍቀድ አለብን። (ገላ. 5:22) መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይሖዋ እምነት እንዳለውም ሆነ እንደሚያስፈልገው አይናገርም። ይሖዋ ሁሉን ቻይና ፍጹም ጥበብ ያለው በመሆኑ ዓላማውን ዳር እንዳያደርስ የሚያግደው ምንም ነገር የለም። በሰማይ ያለው አባታችን፣ ቃል የገባቸውን በረከቶች እንደሚያመጣ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ስለሆነ እነዚህን ተስፋዎች ፍጻሜያቸውን እንዳገኙ አድርጎ ይቆጥራቸዋል። በመሆኑም “እነዚህ ነገሮች ተፈጽመዋል!” በማለት ተናግሯል። (ራእይ 21:3-6⁠ን አንብብ።) የክርስቲያኖች እምነት፣ ይሖዋ ምንጊዜም ቃሉን የሚጠብቅ “ታማኝ አምላክ” እንደሆነ ባላቸው እውቀት ላይ የተመሠረተ ነው።—ዘዳ. 7:9

      ከጥንት የእምነት ምሳሌዎች ትምህርት መውሰድ

      4. በቅድመ ክርስትና ዘመን የኖሩ ታማኝ ወንዶችና ሴቶች ምን ተስፋ ነበራቸው?

      4 በዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ የእምነት ምሳሌ የሚሆኑ 16 ወንዶችና ሴቶች ስም ተጠቅሷል። በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ ዘገባ ስለ እነዚህና “በእምነታቸው ምክንያት በመልካም [ስለተመሠከረላቸው]” ሌሎች በርካታ ሰዎች ይናገራል። (ዕብ. 11:39) ሁሉም ቢሆኑ አምላክ፣ ተስፋ የተሰጠበትን “ዘር” እንደሚያስነሳ እንዲሁም ይህ ዘር ሰይጣንንና ተባባሪዎቹን በሙሉ በማጥፋት የይሖዋን ዓላማ እንደሚፈጽም ‘በእርግጠኝነት ይጠብቁ’ ነበር። (ዘፍ. 3:15) እነዚህ ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች በሞት ያንቀላፉት፣ ተስፋ የተሰጠበት “ዘር” ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ሕይወት ለማግኘት የሚያስችል መንገድ ከመክፈቱ በፊት ነው። (ገላ. 3:16) ያም ቢሆን ይሖዋ የገባውን ቃል የሚፈጽም አምላክ በመሆኑ ከሞት ተነስተው ገነት በሆነች ምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ፤ በዚያም ፍጹም ሕይወት ያገኛሉ።—መዝ. 37:11፤ ኢሳ. 26:19፤ ሆሴዕ 13:14

  • በተስፋችሁ ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ጥቅምት
    • 7. ይሖዋ እምነታችን ምንጊዜም ጠንካራ እንዲሆን እኛን ለመርዳት ምን ዝግጅቶች አድርጎልናል? ከእኛስ ምን ይጠበቃል?

      7 ይሖዋ፣ እምነታችን ምንጊዜም ጠንካራ እንዲሆን እኛን ለመርዳት ሲል ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን በደግነት ሰጥቶናል። “ደስተኛ” እና ‘ስኬታማ’ ለመሆን ከፈለግን የአምላክን ቃል አዘውትረን ከተቻለም በየዕለቱ ማንበብ አለብን። (መዝ. 1:1-3፤ የሐዋርያት ሥራ 17:11⁠ን አንብብ።) በተጨማሪም በቅድመ ክርስትና ዘመን እንደኖሩት የይሖዋ አገልጋዮች፣ አምላክ ቃል በገባቸው ነገሮች ላይ ማሰላሰል እንዲሁም የእሱን ትእዛዛት መጠበቅ አለብን። ይሖዋ ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ አማካኝነት የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ ይሰጠናል። (ማቴ. 24:45) ይሖዋ ከሚያቀርብልን መንፈሳዊ ማዕድ የምንመገብ ከሆነ የመንግሥቱን ተስፋ ‘በእርግጠኝነት እንደጠበቁት’ በጥንት ዘመን የኖሩ የእምነት ምሳሌዎች እንሆናለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ