የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እምነት ከማጣት ተጠበቁ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ሐምሌ 15
    • ከሙሴ የሚበልጥ

      8. ጳውሎስ በዕብራውያን 3:​1 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ሲናገር መሰል ክርስቲያኖች ምን እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ነበር?

      8 ጳውሎስ አንድ አስፈላጊ የሆነ ነጥብ በመጥቀስ “የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ” ሲል ጽፏል። (ዕብራውያን 3:​1) ‘መመልከት’ (በእንግሊዝኛ ኮንሲደር) የሚለው ቃል “በግልጽ መገንዘብ . . .፣ ሙሉ በሙሉ መረዳትና በቅርብ መመልከት” የሚል ትርጉም አለው። (ቫይንስ ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኦልድ ኤንድ ኒው ቴስታመንት ወርድስ) በመሆኑም ጳውሎስ የእምነት አጋሮቹ ኢየሱስ በእምነታቸውና በመዳናቸው ረገድ ለተጫወተው ሚና እውነተኛ አድናቆት ለማሳየት ትጋት የታከለበት ጥረት እንዲያደርጉ አሳስቧቸዋል። ይህን ማድረጋቸው በእምነት ጸንተው ለመቆም ያደረጉትን ውሳኔ ያጠነክርላቸዋል። ታዲያ የኢየሱስ ሚና ምንድን ነው? እሱን ‘መመልከት’ የሚኖርብንስ ለምንድን ነው?

      9. ጳውሎስ ኢየሱስን “ሐዋርያ” እና “ሊቀ ካህናት” ብሎ የጠራው ለምን ነበር?

      9 ጳውሎስ ኢየሱስን “ሐዋርያ” እና “ሊቀ ካህናት” ብሎ ጠርቶታል። የተላከ የሚል ትርጉም ያለው “ሐዋርያ” የሚለው ቃል በዚህ አገባቡ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር የሐሳብ ግንኙነት የሚያደርግበትን መንገድ ያመለክታል። “ሊቀ ካህናት” ሰዎች ወደ አምላክ መቅረብ የሚችሉበት የመገናኛ መስመር ነው። እነዚህ ሁለት ዝግጅቶች ለእውነተኛ አምልኮ እጅግ አስፈላጊ ሲሆኑ ኢየሱስ ደግሞ ሁለቱንም በተሻለ ሁኔታ አቅፎ ይዟል። ስለ አምላክ እውነት የሆነውን ነገር ለሰው ልጆች እንዲያስተምር ከሰማይ የተላከው እሱ ነበር። (ዮሐንስ 1:​18፤ 3:​16፤ 14:​6) በተጨማሪም ኢየሱስ በይሖዋ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ዝግጅት ውስጥ ኃጢአትን እንዲያስተሰርይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ነው። (ዕብራውያን 4:​14, 15፤ 1 ዮሐንስ 2:​1, 2) በኢየሱስ አማካኝነት የምናገኛቸውን በረከቶች ከልብ የምናደንቅ ከሆነ በእምነት ጸንቶ ለመቀጠል የሚያስፈልገው ድፍረትና ቆራጥነት ይኖረናል።

  • እምነት ከማጣት ተጠበቁ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ሐምሌ 15
    • 11, 12. ጳውሎስ ምን ነገርን ‘እስከ መጨረሻው አጽንተው እንዲጠብቁ’ ዕብራውያን ክርስቲያኖችን አሳስቧቸዋል? እኛስ ይህን ምክር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን?

      11 በእርግጥም ዕብራውያን ክርስቲያኖች ከፍተኛ ሞገስ አግኝተው ነበር። ጳውሎስ “የሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች” መሆናቸውን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል፤ ይህ ደግሞ የአይሁድ ሥርዓት ሊሰጣቸው ከሚችለው ነገር ሁሉ ይበልጥ ውድ የሆነ መብት ነው። (ዕብራውያን 3:​1) የጳውሎስ ቃላት እነዚያ የተቀቡ ክርስቲያኖች በአይሁዳዊነታቸው ሊያገኟቸው የሚችሏቸውን ነገሮች በመተዋቸው ከማዘን ይልቅ ለአዲስ ውርሻ በመታጨት ላገኙት መብት አመስጋኞች እንዲሆኑ አድርገዋቸው መሆን አለበት። (ፊልጵስዩስ 3:​8) ጳውሎስ ያገኙትን መብት አጥብቀው እንዲይዙት እንጂ አቅልለው እንዳይመለከቱት ሲያሳስባቸው እንዲህ ብሏል:- “ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ [በአምላክ ቤት] ላይ የታመነ ነው፤ እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።”​—⁠ዕብራውያን 3:​6

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ