-
“እውነተኛ መሠረት ያላትን ከተማ” እየተጠባበቅህ ነው?መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ነሐሴ
-
-
አብርሃም ይሖዋ ቃል በገባቸው ነገሮች ላይ እምነት እንዳለው ያሳየው እንዴት ነው? (አንቀጽ 5ን ተመልከት)
5. አብርሃም፣ አምላክ ንድፍ ያወጣላትን ከተማ ይጠባበቅ እንደነበር እንዴት እናውቃለን?
5 አብርሃም፣ አምላክ ንድፍ ያወጣላትን ከተማ ወይም መንግሥት ይጠባበቅ እንደነበር ያሳየው እንዴት ነው? አንደኛ፣ የየትኛውም ምድራዊ መንግሥት ዜጋ አልሆነም። በአንድ ቦታ ላይ ሰፍሮ ከመኖርና ለየትኛውም ሰብዓዊ ንጉሥ ድጋፍ ከመስጠት ይልቅ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ይኖር ነበር። ከዚህም ሌላ አብርሃም የራሱን መንግሥት ለማቋቋም አልሞከረም። ከዚህ ይልቅ ምንጊዜም ይሖዋን ይታዘዝና እሱ የገባለትን ቃል እስኪፈጽም ይጠባበቅ ነበር። አብርሃም ይህን ማድረጉ በይሖዋ ላይ አስደናቂ እምነት እንደነበረው ያሳያል። አብርሃም ያጋጠሙትን አንዳንድ ፈተናዎች እንዲሁም ከእሱ ምሳሌ የምናገኛቸውን ትምህርቶች እስቲ እንመልከት።
-
-
“እውነተኛ መሠረት ያላትን ከተማ” እየተጠባበቅህ ነው?መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ነሐሴ
-
-
7. አብርሃም፣ እሱንም ሆነ ቤተሰቡን ይሖዋ እንደሚጠብቃቸው መተማመን ያስፈለገው ለምን ነበር?
7 አብርሃም፣ እሱንም ሆነ ቤተሰቡን ይሖዋ እንደሚጠብቃቸው መተማመን ያስፈልገው ነበር። ለምን? አብርሃምና ሣራ በዑር ከተማ የነበራቸውን ምቹ ቤትና ከስጋት ነፃ የሆነ ሕይወት ትተው በከነአን ሜዳዎች ላይ ድንኳን ውስጥ መኖር እንደጀመሩ እናስታውስ። አብርሃምና ቤተሰቡ አሁን የመረጡት ሕይወት፣ ግዙፍ በሆነ ግንብ በታጠረና በውኃ በተከበበ ከተማ የመኖርን ያህል ጥበቃ አያስገኝም። እንዲያውም ለጠላት ጥቃት የተጋለጡ ነበሩ።
8. በአንድ ወቅት አብርሃም ምን ችግር አጋጥሞት ነበር?
8 አብርሃም የአምላክን ፈቃድ ቢያደርግም በአንድ ወቅት ቤተሰቡን ለመመገብ ተቸግሮ ነበር። ይሖዋን ታዝዞ በሄደበት ምድር ላይ ከባድ ረሃብ ተከሰተ። ረሃቡ በጣም ስለከፋ አብርሃም ቤተሰቡን ይዞ ለጊዜው በግብፅ ለመኖር ወሰነ። ሆኖም በግብፅ እያሉ፣ የአገሪቱ ገዢ የሆነው ፈርዖን ሚስቱን ወሰደበት። ይሖዋ ጣልቃ ገብቶ ፈርዖን ሣራን እንዲመልሳት እስኪያደርግ ድረስ አብርሃም ምን ያህል ተጨንቆ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም።—ዘፍ. 12:10-19
9. አብርሃም በቤተሰቡ ውስጥ ምን ችግሮች አጋጥመውታል?
9 አብርሃም በቤተሰብ ሕይወቱም ችግሮች አጋጥመውት ነበር። የሚወዳት ሚስቱ ሣራ፣ ልጅ መውለድ አልቻለችም። ለበርካታ አሥርተ ዓመታት፣ ይህን ስሜት የሚጎዳ ሁኔታ ተቋቁመው መኖር ነበረባቸው። ከጊዜ በኋላ ሣራ፣ አገልጋይዋን አጋርን ለአብርሃም ሰጠችው፤ ይህን ያደረገችው ልጆች እንድትወልድላቸው አስባ ነበር። ይሁንና አጋር፣ እስማኤልን ስትፀንስ ሣራን መናቅ ጀመረች። ሣራ ሁኔታው በጣም ስለከበዳት አጋርን እንድትኮበልል አደረገቻት።—ዘፍ. 16:1-6
10. አብርሃም ከእስማኤልም ሆነ ከይስሐቅ ጋር በተያያዘ በይሖዋ መተማመን እንዲያስፈልገው ያደረጉ ምን ሁኔታዎች አጋጥመውታል?
10 በመጨረሻም ሣራ ፀነሰችና ወንድ ልጅ ወለደች፤ አብርሃምም ልጁን ይስሐቅ ብሎ ሰየመው። አብርሃም፣ እስማኤልንም ሆነ ይስሐቅን ይወዳቸው ነበር። ይሁን እንጂ እስማኤል በይስሐቅ ላይ ባደረገበት ነገር የተነሳ አብርሃም እስማኤልንና አጋርን ከቤት ለማስወጣት ተገደደ። (ዘፍ. 21:9-14) በኋላ ላይ ደግሞ ይሖዋ፣ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብለት አብርሃምን ጠየቀው። (ዘፍ. 22:1, 2፤ ዕብ. 11:17-19) በሁለቱም ወቅቶች አብርሃም፣ ልጆቹን በተመለከተ ይሖዋ የገባውን ቃል መፈጸሙ እንደማይቀር መተማመን አስፈልጎት ነበር።
11. አብርሃም ይሖዋን በትዕግሥት መጠባበቅ ያስፈለገው ለምን ነበር?
11 በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ አብርሃም ይሖዋን በትዕግሥት መጠባበቅ አስፈልጎት ነበር። ቤተሰቡን ይዞ ከዑር ሲወጣ ዕድሜው ከ70 ዓመት በላይ የነበረ ይመስላል። (ዘፍ. 11:31 እስከ 12:4) ከዚያም መቶ ገደማ ለሚሆኑ ዓመታት በከነአን ምድር ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ድንኳን ውስጥ ኖሯል። አብርሃም የሞተው በ175 ዓመቱ ነው። (ዘፍ. 25:7) ሆኖም የተዘዋወረባትን ምድር ለዘሮቹ እንደሚሰጥ ይሖዋ የገባለት ቃል ሲፈጸም ለማየት አልበቃም። ይጠብቃት የነበረችው ከተማ ማለትም የአምላክ መንግሥት ስትቋቋምም አላየም። ያም ቢሆን አብርሃም “በሕይወቱ ረክቶና ዕድሜ ጠግቦ” እንደሞተ ተገልጿል። (ዘፍ. 25:8) አብርሃም ብዙ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙትም እምነቱ ምንጊዜም ጠንካራ ነበር፤ ይሖዋን በትዕግሥት ለመጠባበቅም ፈቃደኛ ነበር። አብርሃም መጽናት የቻለው ለምንድን ነው? በሕይወቱ በሙሉ ይሖዋ ጥበቃ ስላደረገለትና እንደ ወዳጁ አድርጎ ስለተንከባከበው ነው።—ዘፍ. 15:1፤ ኢሳ. 41:8፤ ያዕ. 2:22, 23
-