-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 58—ዕብራውያን“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 17
-
-
26 የዕብራውያን መልእክት በግልጽ እንደሚናገረው አብርሃም የአምላክን መንግሥት ማለትም “መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር።” ይህች ከተማ “ሰማያዊ አገር” ናት። አብርሃም “በእምነት” የአምላክን መንግሥት አሻግሮ የተመለከተ ሲሆን “የተሻለውን ትንሣኤ” አግኝቶ በረከቶችን ማጨድ ይችል ዘንድ ታላላቅ መሥዋዕቶችን ከፍሏል። የአብርሃም እምነትም ሆነ ጳውሎስ በዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ የዘረዘራቸው ‘እንደ ደመና በዙሪያችን ያሉ’ ብዙ ታማኝ ምስክሮች ያሳዩት እምነት እንዴት ያለ ግሩም ምሳሌ ይሆነናል! ይህን ዘገባ ስናነብ፣ እነዚህ ንጹሕ አቋም ጠባቂዎች ያላቸው ዓይነት መብትና ተስፋ እኛም በማግኘታችን ልባችን በምስጋናና በደስታ ይሞላል። በመሆኑም “በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት [እንድንሮጥ]” ተበረታተናል።—11:8, 10, 16, 35፤ 12:1
-