-
በተስፋችሁ ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ጥቅምት
-
-
10. ንጹሕ አቋማቸውን ለማላላት ፈቃደኛ ያልሆኑ የአምላክ አገልጋዮችን ምሳሌ ጥቀስ። እንዲህ ለማድረግ ኃይል ያገኙት እንዴት ነው?
10 በዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በስም ያልተጠቀሱ በርካታ የአምላክ አገልጋዮች በጽናት የተወጧቸውን መከራዎች ዘርዝሯል። ለአብነት ያህል፣ ሐዋርያው ልጆቻቸውን በሞት ስላጡና በኋላም በትንሣኤ ስለተቀበሉ የእምነት ምሳሌ የሚሆኑ ሴቶች ጠቅሷል። በተጨማሪም “ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ” ሌሎች የአምላክ አገልጋዮች ገልጿል፤ እነዚህ ሰዎች “ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው።” (ዕብ. 11:35) ጳውሎስ ይህን የተናገረው እነማንን በአእምሮው ይዞ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ባንችልም አምላክን በመታዘዛቸውና የእሱን ፈቃድ በመፈጸማቸው በድንጋይ ተወግረው ስለሞቱት ስለ ናቡቴ እና ስለ ዘካርያስ መናገሩ ሊሆን ይችላል። (1 ነገ. 21:3, 15፤ 2 ዜና 24:20, 21) ዳንኤልና ጓደኞቹም ንጹሕ አቋማቸውን ቢያላሉ “ነፃ መሆን” የሚችሉበት አጋጣሚ ነበራቸው። እነዚህ ወጣቶች በአምላክ ኃይል ላይ እምነት ስለነበራቸው “የአንበሶችን አፍ ዘግተዋል” እንዲሁም “የእሳትን ኃይል አጥፍተዋል” ሊባልላቸው ችሏል።—ዕብ. 11:33, 34፤ ዳን. 3:16-18, 20, 28፤ 6:13, 16, 21-23
-
-
በተስፋችሁ ላይ ያላችሁን እምነት አጠናክሩመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ጥቅምት
-
-
12. ፈተናዎችን በጽናት በመወጣት ረገድ ከሁሉ የላቀ ምሳሌ የተወው ማን ነው? ለመጽናት የረዳውስ ምንድን ነው?
12 ጳውሎስ የእምነት ምሳሌ የሚሆኑ የተለያዩ ወንዶችንና ሴቶችን ከዘረዘረ በኋላ ከሁሉ የላቀ አርዓያ ስለሆነው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተናግሯል። ዕብራውያን 12:2 “ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል፣ የሚደርስበትን ውርደት ከምንም ሳይቆጥር በመከራ እንጨት ላይ እስከ መሞት ድረስ ጸንቷል፤ እንዲሁም በአምላክ ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል” ይላል። በእርግጥም፣ ኢየሱስ በጣም ከባድ ፈተናዎችን በመቋቋም የተወውን የእምነት ምሳሌ ‘በጥሞና ማሰብ’ ይኖርብናል። (ዕብራውያን 12:3ን አንብብ።) እንደ አንቲጳስ ያሉ በጥንት ዘመን የነበሩና ሰማዕት የሆኑ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል በንጹሕ አቋማቸው ጸንተዋል። (ራእይ 2:13) በመሆኑም እነዚህ የአምላክ አገልጋዮች የላቀ ትንሣኤ ያገኛሉ፤ ይኸውም ከሞት ተነስተው በሰማይ ይኖራሉ፤ ይህ ደግሞ የጥንቶቹ የእምነት ሰዎች ተስፋ ያደርጉት ከነበረው “የተሻለ ትንሣኤ” እንኳ የበለጠ ነው። (ዕብ. 11:35) በሞት አንቀላፍተው የነበሩት ታማኝ ቅቡዓን በሙሉ፣ የአምላክ መንግሥት በ1914 ከተወለደ ብዙም ሳይቆይ ከሞት ተነስተው መንፈሳዊ ሕይወት ተቀብለዋል፤ እነዚህ ቅቡዓን ከኢየሱስ ጋር ሆነው በሰው ልጆች ላይ ይገዛሉ።—ራእይ 20:4
-