የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከምታያቸው ነገሮች ባሻገር ተመልከት!
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | የካቲት 15
    • ኢየሱስ ሌሎች ሰዎች ሲሠቃዩ ከማየቱም በላይ በራሱም ላይ መከራ ደርሶበታል። (ዕብራውያን 5:7, 8) ይሁን እንጂ ፍጹም የሆነ መንፈሳዊ የማየት ችሎታ ስለ ነበረው የጸና አቋም በመያዝ የሚያገኘውን የላቀ የማይጠፋ ሕይወት ሽልማት አሻግሮ ተመልክቷል። በዚያን ጊዜ መሲሐዊ ንጉሥ ሆኖ የተጨነቁት የሰው ልጆች ካሉበት ጎስቋላ ሁኔታ የይሖዋ የመጀመሪያ ዓላማ ወደ ነበረው ፍጽምና የመመለስ መብት ይኖረዋል። እነዚህን የማይታዩ የወደፊት ተስፋዎች በዓይነ ሕሊናው አተኩሮ በመመልከቱ የማያቋርጡ መከራዎች ቢያጋጥሙትም ከአምላክ አገልግሎት ደስታ እንዲያገኝ አስችሎታል። ጳውሎስ ከዚህ ቆየት ብሎ “እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል [“በመከራ እንጨት” አዓት] ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል” በማለት ጽፏል።—ዕብራውያን 12:2

  • ከምታያቸው ነገሮች ባሻገር ተመልከት!
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | የካቲት 15
    • ኢየሱስ እንዲጸና ስላስቻለው ነገር ጳውሎስ በሚጽፍበት ወቅት “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፣ [“አትኩረን በመመልከት፣” አዓት] በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ” በማለት ልንከተለው የሚገባንን አካሄድ ጠቁሞናል። (ዕብራውያን 12:1, 2) አዎን፣ ክርስቲያናዊ ሩጫችንን በተሳካ ሁኔታና በደስታ ለመሮጥ ከፊታችን ካሉት ነገሮች ባሻገር መመልከት ይኖርብናል። ይሁን እንጂ ኢየሱስን ‘አትኩረን መመልከት’ የምንችለው እንዴት ነው? እንዲህ ማድረጋችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?

      አንደኛ ኢየሱስ በ1914 የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ በሰማይ በመግዛት ላይ ነው። እርግጥ ይህ በሥጋዊ ዓይናችን የሚታይ ነገር አይደለም። ሆኖም ኢየሱስን ‘አትኩረን ከተመለከትን’ መንፈሳዊ የማየት ችሎታችን እርሱ በአሁኑ ወቅት ይህን ክፉ ሥርዓት ለማጥፋትና ሰይጣንንና አጋንንታዊ ጭፍሮቹን ከማንኛውም እንቅስቃሴ ለማገድ እንደ ተዘጋጀ እንድንመለከት ያስችለናል። አሁንም ይበልጥ አሻግረን ስንመለከት መንፈሳዊ የማየት ችሎታችን ‘ሞት፣ ኀዘን፣ ጨኸት ወይም ሥቃይ የማይኖርበትንና የቀደመው ሥርዓት የሚያልፍበትን’ አስደሳች አዲስ ዓለም ያሳየናል።—ራእይ 19:11-16፤ 20:1-3፤ 21:4

      ስለዚህ በየቀኑ ሊያጋጥሙን በሚችሉት ጊዜ ­ያዊ ችግሮች በጣም ከመጨነቅ ይልቅ ዓይናችንን ዘላለማዊ በሆኑት ነገሮች ላይ ለምን አንተክልም? በእምነት ዓይናችን በዚች በተበከለችዋ ምድር ላይ ካለው በሽታና ስግብግብነት ባሻገር በማየት ጤናሞች፣ ደስተኞችና አሳቢ በሆኑ ሰዎች የምትሞላውን ገነት ለምን አንመለከትም? ከአካላዊና መንፈሳዊ ጉድለቶቻችን ባሻገር በመመልከት በክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ከእነዚህ ነገሮች ለዘላለም ነፃ የምንሆንበትን ጊዜ ለምን አናይም? በጦርነት፣ በወንጀልና በዓመፅ ከሚከሰተው ታላቅ እልቂት ባሻገር በማየት ከሞት የተነሡ ሰዎች የይሖዋን ጽድቅና ሰላም ሲማሩ ለምን አትመለከትም?

      ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስን ‘አትኩሮ መመልከት’ መንፈሳዊ የማየት ችሎታችንን ተጠቅመን የአምላክ መንግሥት በዓይን የማይታይ ቢሆንም እንኳ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ በሚገኙት የአምላክ ሕዝቦች መካከል የፈጠረውን አንድነት፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ የወንድማማች መዋደድና መንፈሳዊ ብልጽግና በትኩረት መመልከትን ይጨምራል። በጀርመን የምትገኝ አንዲት ክርስቲያን ዩናይትድ ባይ ዲቫይን ቲቺንግ የተባለውን የቪዲዮ ካሴት ከተመለከተች በኋላ እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “የቪዲዮ ካሴቱ በመላው ዓለም የሚገኙ ብዙ ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች ከሕዝብ ተቃውሞ ቢያጋጥማቸውም እንኳ በአሁኑ ጊዜ ይሖዋን በታማኝነት በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ይበልጥ እንዳሰላስል ረድቶኛል። ዓመፅና ጥላቻ በሞላበት ዓለም ውስጥ ይህን የመሰለ የወንድማማች አንድነት ማግኘት ምንኛ ውድ ነው!”

      ይሖዋ፣ ኢየሱስ፣ ታማኞች መላእክትና በሚልዮን የሚቆጠሩ መሰል ክርስቲያኖች ከጎንህ እንዳሉ ‘ይታይሃልን’? ይህ የሚታይህ ከሆነ ተስፋ ቆርጠህ እድገት እንዳታደርግና በክርስቲያናዊ አገልግሎት ‘የማታፈራ’ እንድትሆን ሊያደርግህ በሚችለው ‘በዚህ ዓለም አሳብ’ ከመጠን በላይ አትጨነቅም። (ማቴዎስ 13:22) ስለዚህ መንፈሳዊ ዓይንህን በተቋቋመው የአምላክ መንግሥትና ይህ መንግሥት አሁንም ሆነ ወደፊት በሚያመጣቸው በረከቶች ላይ በመትከል ኢየሱስን ‘አትኩረህ ተመልከት።’

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ