-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥራና ስለ ገንዘብ ምን ይላል?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. ለገንዘብ ሊኖረን የሚገባው ሚዛናዊ አመለካከት ምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ “ገንዘብ ጥበቃ እንደሚያስገኝ” ይናገራል፤ በሌላ በኩል ግን ገንዘብ ብቻውን ደስተኛ ሊያደርገን እንደማይችል ያስጠነቅቃል። (መክብብ 7:12) የአምላክ ቃል ገንዘብ እንዳንወድ፣ ከዚህ ይልቅ ‘ባሉን ነገሮች ረክተን እንድንኖር’ የሚያበረታታን ለዚህ ነው። (ዕብራውያን 13:5ን አንብብ።) ባሉን ነገሮች ረክተን የምንኖር ከሆነ ‘ተጨማሪ ነገር ማግኘት አለብኝ’ የሚለው ስሜት ከሚያስከትለው ብስጭት ነፃ እንሆናለን። አላስፈላጊ ዕዳ ውስጥ ከመግባት እንድናለን። (ምሳሌ 22:7) በተጨማሪም ቁማር ከመጫወትና በአጭር ጊዜ ለመክበር ያስችላሉ የሚባሉ የንግድ አማራጮችን ከማሳደድ እንቆጠባለን።
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሥራና ስለ ገንዘብ ምን ይላል?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
5. ባሉን ነገሮች ረክተን መኖራችን ይጠቅመናል
በርካታ ሰዎች የቻሉትን ያህል ብዙ ገንዘብ ለማጠራቀም ይሞክራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከዚህ የተለየ ነገር እንድናደርግ ይመክረናል። አንደኛ ጢሞቴዎስ 6:6-8ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንድናደርግ ይመክረናል?
ያለን ገንዘብ በጣም አነስተኛ ቢሆንም እንኳ ደስተኛ መሆን እንችላለን። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
በቪዲዮው ላይ የታዩት ቤተሰቦች ያላቸው ገንዘብ ጥቂት ቢሆንም ደስተኛ እንዲሆኑ የረዳቸው ምንድን ነው?
ብዙ ገንዘብ እያለንም ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት የምንፈልግ ቢሆንስ? ኢየሱስ ይህ ያለውን አደጋ የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል። ሉቃስ 12:15-21ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ኢየሱስ ከሰጠው ምሳሌ ምን ትምህርት አግኝተሃል?—ቁጥር 15ን ተመልከት።
ምሳሌ 10:22ን እና 1 ጢሞቴዎስ 6:10ን አንብቡና አወዳድሩ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ምን ይመስልሃል? የይሖዋ ወዳጅ መሆን ወይስ ብዙ ገንዘብ ማግኘት? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
ገንዘብ ማሳደድ ምን ችግሮች ሊያስከትል ይችላል?
-