የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 1 ገጽ 8-9
  • በሕይወት እርካታ ለማግኘት የሚረዳ ቁልፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በሕይወት እርካታ ለማግኘት የሚረዳ ቁልፍ
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትጉ ሠራተኛ ሁን
  • ሐቀኛ ሁን
  • ለገንዘብ ትክክለኛ አመለካከት ይኑርህ
  • ከሁሉ የተሻለውን ትምህርት ምረጥ
  • ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት ይኑርህ
    ንቁ!—2015
  • ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ገንዘብ
    ንቁ!—2014
  • ለገንዘብ ሊኖረን የሚገባው ተገቢ አመለካከት ምንድን ነው?
    ንቁ!—2007
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 1 ገጽ 8-9
ሕንድ ውስጥ አንድ እናትና ልጅ ውድ ነገሮች በሚሸጡባቸው ሱቆች አጠገብ ሲያልፉ። ሌሎች ሰዎች ዕቃዎቹን ለማግኘት እየቋመጡ ቢሆንም እነሱ ግን ባላቸው ነገር ረክተዋል።

በሕይወት እርካታ ለማግኘት የሚረዳ ቁልፍ

ወጣት አረጋዊ፣ ያገባ ያላገባ ሳይል ሁላችንም በሕይወታችን ደስታና እርካታ ማግኘት እንፈልጋለን። ፈጣሪያችንም በሕይወታችን እርካታ እንድናገኝ ይፈልጋል፤ ስለዚህ በዚህ ረገድ የሚረዳን ጠቃሚ ምክር ሰጥቶናል።

ትጉ ሠራተኛ ሁን

“ለተቸገረ ሰው የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በእጆቹ መልካም ተግባር እያከናወነ በትጋት ይሥራ።”—ኤፌሶን 4:28

ፈጣሪያችን ሥራን እንዳንጠላ ያበረታታናል። ለምን? ተግቶ የሚሠራ ሰው ደስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ራሱን ማስተዳደርም ሆነ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ነገር ማቅረብ ይችላል። እንዲያውም ከራሱ አልፎ የተቸገሩትን መርዳት ይችል ይሆናል። በአሠሪው ዘንድ ተፈላጊ ይሆናል። ስለዚህ ትጉ ሠራተኛ ከሥራ የመባረር አጋጣሚው ጠባብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ተግቶ መሥራት የሚያስገኘው መልካም ውጤት “የአምላክ ስጦታ” እንደሆነ መናገሩ አያስገርምም።—መክብብ 3:13

ሐቀኛ ሁን

“ሐቀኛ ሕሊና እንዳለን እናምናለን፤ ደግሞም በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን።”—ዕብራውያን 13:18

ሐቀኛ ከሆንን ለራሳችን አክብሮት ይኖረናል፤ የአእምሮ ሰላም እናገኛለን እንዲሁም ጥሩ እንቅልፍ እንተኛለን። በተጨማሪም በሌሎች ዘንድ አክብሮትና አመኔታ እናተርፋለን። ሐቀኛ ያልሆኑ ሰዎች፣ እነዚህን መልካም ነገሮች ራሳቸውን ይነፍጋሉ። ሕሊናቸው ይረብሻቸዋል፤ እንዲሁም ‘ያደረግኩት ነገር ቢታወቅብኝስ’ በሚል ስጋት ይኖራሉ።

ለገንዘብ ትክክለኛ አመለካከት ይኑርህ

“አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ።”—ዕብራውያን 13:5

ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ለማግኘት ገንዘብ ያስፈልገናል። ይሁንና ‘የገንዘብ ፍቅር’ በጣም አደገኛ ነው። ገንዘብ የሚወድ ሰው፣ ብዙ ገንዘብ ለማግኘት የሚያደርገው ሩጫ ጊዜውንና ጉልበቱን ሁሉ ያሟጥጥበታል። ገንዘብ ለማግኘት ሲሯሯጥ ትዳሩ ላይ ውጥረት ሊፈጠር ይችላል፤ ከልጆቹ ጋር የሚያሳልፈው ጊዜ ያጣል፤ አልፎ ተርፎም ጤንነቱ ሊጎዳ ይችላል። (1 ጢሞቴዎስ 6:9, 10) ከዚህም አልፎ፣ የገንዘብ ፍቅር ያለው ሰው ለማጭበርበር ሊፈተን ይችላል። አንድ ጠቢብ ሰው እንዲህ ብሏል፦ “ታማኝ ሰው ብዙ በረከት ያገኛል፤ ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ንጽሕናውን ማጉደፉ አይቀርም።”—ምሳሌ 28:20

ከሁሉ የተሻለውን ትምህርት ምረጥ

“ጥበብንና የማመዛዘን ችሎታን ጠብቅ።”—ምሳሌ 3:21

ጥሩ ትምህርት መከታተላችን፣ አዋቂ ስንሆን ኃላፊነት የሚሰማን ሰዎችና ወላጆች እንድንሆን ይረዳናል። ይሁንና ትምህርት ቤት የሚሰጠው ትምህርት ብቻውን በሕይወት ስኬታማና ደስተኛ ለመሆን ዋስትና አይሆንም። በሁሉም የሕይወታችን ዘርፍ ስኬታማ መሆን ከፈለግን ከአምላክ የሚገኘውን ትምህርት መማር ያስፈልገናል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክን ስለሚሰማ ሰው ሲናገር “የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል” ይላል።—መዝሙር 1:1-3

በሕይወቴ ደስታና እርካታ አግኝቻለሁ

“ባለሁበት አካባቢ፣ ብዙ ሰዎች ሰፋ ያለ ትምህርት ለመከታተል እንዲሁም ሀብትና ዝና ለማግኘት ብዙ ሲደክሙ አያለሁ። ሆኖም ያሰቡት ግብ ላይ ከደረሱ በኋላም እንኳ ደስታ ሲርቃቸው አስተውያለሁ። እኔ ግን መጽሐፍ ቅዱስን መማሬ ትክክለኛ አመለካከት እንድይዝ ረድቶኛል። ገንዘብ በአንዳንድ አቅጣጫዎች ጥበቃ ሊሆንልን ቢችልም ደስታ ወይም እውነተኛ ፍቅር ሊገዛልን እንደማይችል ተምሬያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብንና ሥራን በተመለከተ ጥበብ ያለበት ውሳኔ እንዳደርግ ረድቶኛል፤ ስለዚህ በሕይወቴ ደስታና እርካታ አግኝቻለሁ።”—ኪሾር

ኪሾር።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፦

ሥራን፣ ገንዘብንና ትምህርትን በተመለከተ ፈጣሪያችን የሰጠንን ሌሎች ምክሮች ማወቅ ትፈልጋለህ? jw.org የተባለው ድረ ገጽ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ሰላም እና ደስታ በሚለው ሥር ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ