የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ”
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
    • “በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ” የተባልነው ለምንድን ነው?

      9 ‘በመካከላችን ሆነው አመራር የሚሰጡትን የምናስብበትና’ በእነሱ ላይ እምነት እንዳለን የምናሳይበት ብዙ ምክንያት አለን። እንዲህ ማድረጋችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፦ “ተግተው ስለሚጠብቋችሁና ይህን በተመለከተ ስሌት ስለሚያቀርቡ በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ እንዲሁም ተገዙ፤ ይህን የምታደርጉት ሥራቸውን በደስታ እንጂ በሐዘን እንዳያከናውኑ ነው፤ አለዚያ ሥራቸውን የሚያከናውኑት በሐዘን ይሆናል፤ ይህ ደግሞ እናንተን ይጎዳችኋል።” (ዕብ. 13:17) መንፈሳዊ ጥበቃ ስለሚያደርጉልንና ለመንፈሳዊ ደህንነታችን ስለሚያስቡ አመራር የሚሰጡንን መታዘዛችንና ለእነሱ መገዛታችን ወሳኝ ነገር ነው።

      10 በአንደኛ ቆሮንቶስ 16:14 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ጳውሎስ “የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በፍቅር አድርጉ” ብሏል። ከአምላክ ሕዝቦች ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ውሳኔዎች ከሁሉ በላቀው የፍቅር ባሕርይ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። አንደኛ ቆሮንቶስ 13:4-8 ስለ ፍቅር ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይቀናም። ጉራ አይነዛም፣ አይታበይም፣ ጨዋነት የጎደለው ምግባር አያሳይም፣ የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም፣ በቀላሉ አይበሳጭም። ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም። ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም፤ ከዚህ ይልቅ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል። ሁሉን ችሎ ያልፋል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ ሁሉን ነገር በጽናት ይቋቋማል። ፍቅር ለዘላለም ይኖራል።” ለይሖዋ አገልጋዮች ጥቅም ሲባል የሚደረጉ ውሳኔዎች በሙሉ በፍቅር ላይ የተመሠረቱ በመሆናቸው እንዲህ ባለው አመራር ላይ እምነት የምንጥልበት በቂ ምክንያት አለን። ደግሞም ይህ የይሖዋ ፍቅር መገለጫ ነው።

      ለመንፈሳዊ ደህንነታችን ለሚያስቡት ወንድሞች መገዛታችን ወሳኝ ነገር ነው

      11 በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ይሖዋ ሕዝቡን ለመምራት የሚጠቀመው ፍጽምና በሚጎድላቸው ሰዎች ነው። ቀደም ባሉት ዘመናትም ይሖዋ ፈቃዱን ለማስፈጸም የተጠቀመው ፍጽምና በጎደላቸው ሰዎች ነበር። ኖኅ መርከብ ሠርቷል፤ እንዲሁም በዘመኑ ስለሚመጣው ጥፋት ሰብኳል። (ዘፍ. 6:13, 14, 22፤ 2 ጴጥ. 2:5) ሙሴ ደግሞ የይሖዋን ሕዝብ ከግብፅ ምድር እየመራ እንዲያወጣ ተሹሞ ነበር። (ዘፀ. 3:10) መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ መሪነት የጻፉት ፍጽምና የጎደላቸው ሰዎች ናቸው። (2 ጢሞ. 3:16፤ 2 ጴጥ. 1:21) በመሆኑም ይሖዋ በዛሬው ጊዜ የስብከቱንና ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ሥራ ለመምራት ፍጽምና በጎደላቸው ሰዎች መጠቀሙ በአምላክ ድርጅት ላይ ያለንን እምነት አያዳክመውም። ከዚህ ይልቅ ድርጅቱ፣ የይሖዋ ድጋፍ ባይኖረው ኖሮ አሁን እያከናወነ ያለውን ነገር መፈጸም እንደማይችል ስለምናውቅ እምነታችን ይጠነክራል። ታማኙ ባሪያ ከባድ መከራ ቢደርስበትም በርካታ ነገሮችን ማከናወን መቻሉ የአምላክ መንፈስ አመራር እንዳልተለየው ያረጋግጣል። በዛሬው ጊዜ ይሖዋ በድርጅቱ ምድራዊ ክፍል ላይ የተትረፈረፈ በረከት እያፈሰሰ ነው። በመሆኑም ይህን ድርጅት በሙሉ ልባችን እንደግፋለን፤ እንዲሁም በድርጅቱ እንተማመናለን።

  • “በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ”
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
    • 14 በድርጅቱ እንደምንተማመን የምናሳይበት ሌላው መንገድ ለሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ድጋፍ መስጠት ነው። ይህ ደግሞ ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች ለምሳሌ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች የሚሰጡትን አመራር በትሕትና መቀበልን ይጨምራል። እነዚህ ወንድሞች ልንታዘዛቸውና ልንገዛላቸው ከሚገቡ “አመራር የሚሰጡ” ወንድሞች መካከል ይገኙበታል። (ዕብ. 13:7, 17) አንዳንድ ውሳኔዎች የተደረጉበትን ምክንያት ሙሉ በሙሉ በማንረዳበት ጊዜም እንኳ ውሳኔዎቹን መደገፋችን ዘላቂ ጥቅም እንደሚያስገኝልን እናውቃለን። ይሖዋም ቃሉንና ድርጅቱን በመታዘዛችን ይባርከናል። በዚህ መንገድ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደምንገዛ እናሳያለን።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ