የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አፍቃሪ ለሆኑት እረኞች በትሕትና ተገዙ
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | ሚያዝያ 1
    • 7. ሐዋርያው ጳውሎስ ለክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች ሊኖረን ስለሚገባው አመለካከት ምን ምክር ሰጥቷል?

      7 በሰማይ ያሉት እረኞቻችን ማለትም ይሖዋ አምላክና ኢየሱስ ክርስቶስ በጉባኤ ውስጥ በኃላፊነት ቦታ ላይ ላስቀመጧቸው የበታች እረኞች እንድንታዘዝና እንድንገዛ ይጠብቁብናል። (1 ጴጥሮስ 5:5) ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ ተነሳስቶ እንደሚከተለው ሲል ጽፏል:- “የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን ዐስቡ፤ የኑሮአቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሉአቸው። ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጒዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው። አለበለዚያ አይበጃችሁም።”—ዕብራውያን 13:7, 17

      8. ጳውሎስ ስለምን ነገር ‘እንድንመለከት’ አበረታቶናል? ‘ታዛዥ’ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

      8 ጳውሎስ፣ ሽማግሌዎች በአኗኗራቸው ታማኝ መሆናቸው ያስገኘላቸውን ውጤት ‘እንድንመለከት’ ወይም በጥንቃቄ እንድንመረምር እንዲሁም በእምነታቸው እንድንመስላቸው አበረታቶናል። ከዚህም በላይ፣ ለእነዚህ የተሾሙ ወንዶች እንድንታዘዝና ለሚሰጡን መመሪያ እንድንገዛ መክሮናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት ሪቻርድ ፍራንስ እንደገለጹት በዚህ ጥቅስ ላይ “ታዘዙ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “መታዘዝን ለማመልከት የሚሠራበት የተለመደው ቃል” አይደለም። “ከዚህ ይልቅ ይህ ቃል በቀጥታ ሲተረጎም ‘አምናችሁ ተቀበሉ’ ማለት ሲሆን ይህም የሽማግሌዎችን የመሪነት ቦታ በፈቃደኝነት መቀበልን ያመለክታል።” ሽማግሌዎችን የምንታዘዘው የአምላክ ቃል እንዲህ እንድናደርግ ስለሚያሳስበን ብቻ ሳይሆን ስለመንግሥቱ ፍላጎትና ስለደህንነታችን ከልብ የሚጨነቁ መሆናቸውን ስለምንገነዘብም ጭምር ነው። የሽማግሌዎችን የመሪነት ቦታ በፈቃደኝነት አምነን መቀበላችን ደስታ እንደሚያመጣልን ጥርጥር የለውም።

  • አፍቃሪ ለሆኑት እረኞች በትሕትና ተገዙ
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | ሚያዝያ 1
    • 10, 11. በመጀመሪያው መቶ ዘመንም ሆነ በዛሬው ጊዜ የበላይ ተመልካቾች ለእምነት አጋሮቻቸው ‘የአምላክን ቃል የተናገሩት’ በምን መንገድ ነው?

      10 ቀደም ሲል በተጠቀሰው ጥቅስ ማለትም በዕብራውያን 13:7, 17 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ለክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች እንድንታዘዝና እንድንገዛ የሚገፋፉንን አራት ምክንያቶች ዘርዝሯል። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ‘የአምላክን ቃል ነግረውናል።’ ኢየሱስ እነዚህን ስጦታ የሆኑ ወንዶች ለጉባኤው የሰጠው “ቅዱሳንን ለአገልግሎት ሥራ ለማዘጋጀት” ወይም ለማስተካከል መሆኑን አትዘንጉ። (ኤፌሶን 4:11, 12) ኢየሱስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩትን ክርስቲያኖች አስተሳሰብና ሥነ ምግባር ለማስተካከል ታማኝ በሆኑ የበታች እረኞች ተጠቅሟል። ከእነዚህ እረኞች መካከል አንዳንዶቹ በመንፈስ ተመርተው ለጉባኤዎች ደብዳቤዎችን ጽፈዋል። ኢየሱስ የጥንት ክርስቲያኖችን ለመምራትና እምነታቸውን ለማጠናከር በመንፈስ በተቀቡት በእነዚህ የበላይ ተመልካቾች ተጠቅሟል።—1 ቆሮንቶስ 16:15-18፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:2፤ ቲቶ 1:5

      11 በዛሬው ጊዜ ኢየሱስ ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ በሚወክሉት በበላይ አካሉና በተሾሙ ሽማግሌዎች አማካኝነት ይመራናል። (ማቴዎስ 24:45 የ1954 ትርጉም) “የእረኞች አለቃ” ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለን አክብሮት፣ ጳውሎስ ‘በእናንተ መካከል በትጋት የሚሠሩትን፣ በጌታም የበላዮቻችሁና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን አክብሯቸው’ በማለት የሰጠንን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ ያነሳሳናል።—1 ጴጥሮስ 5:4፤ 1 ተሰሎንቄ 5:12፤ 1 ጢሞቴዎስ 5:17

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ