-
ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን!መጠበቂያ ግንብ—2005 | ሰኔ 15
-
-
የአምላክ አገልጋዮች “ልዩ ልዩ መከራ” እንደሚደርስባቸው መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። (ያዕቆብ 1:2) እዚህ ላይ “ልዩ ልዩ” (በግሪክኛ ፓይኪሎስ) የሚለውን ቃል ልብ በል። የመጀመሪያው የግሪክኛ ቃል ቀደም ሲል “በርካታ” ወይም “ባለ ብዙ ፈርጅ” የሚል ትርጉም የነበረው ሲሆን “ፈተናዎች ብዙ ገጽታ” ያላቸው መሆኑንም ጎላ አድርጎ ይገልጻል። በቀላል አነጋገር “ብዙ መልክ ያለው” ማለት ነው። በመሆኑም “ልዩ ልዩ መከራ” ሲባል መከራ በተለያየ መልክ እንደሚመጣ ያሳያል። ሆኖም ይሖዋ እያንዳንዱን ፈተና መቋቋም እንድንችል ይደግፈናል። እንዲህ ብለን በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ለምንድን ነው?
-