-
‘ሌሎችን የሚያንጽ መልካም ቃል’ ተናገር‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
7, 8. ስለምንናገረው ነገር በይሖዋ ፊት ምን ያህል ተጠያቂዎች እንሆናለን?
7 አነጋገራችንን መቆጣጠር አስፈላጊ የሚሆንበት ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ስለምንናገራቸው ነገሮች ይሖዋ የሚጠይቀን መሆኑ ነው። አንደበታችንን የምንጠቀምበት መንገድ ከሰዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድናም ይነካብናል። ያዕቆብ 1:26 “አንድ ሰው አምልኮቱን እያከናወነ እንዳለ የሚሰማው ቢሆንም እንኳ አንደበቱን የማይገታ ከሆነ ይህ ሰው የገዛ ልቡን እያታለለ ይኖራል፤ የዚህ ሰው አምልኮም ከንቱ ነው” ይላል።b ከዚህ በፊት በነበረው ምዕራፍ ላይ እንደተመለከትነው አንደበታችንን የምንጠቀምበት መንገድ ከአምልኮታችን ተነጥሎ የሚታይ አይደለም። አንደበታችን ካልተገራ ማለትም ጎጂና መርዛማ ቃላት የሚያወጣ ከሆነ ይሖዋን ለማገልገል የምንለፋው ልፋት ሁሉ በእሱ ዓይን ከንቱ ሊሆንብን ይችላል። ታዲያ ይህ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም?—ያዕቆብ 3:8-10
-
-
‘ሌሎችን የሚያንጽ መልካም ቃል’ ተናገር‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
-
-
b “ከንቱ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ፍሬ ቢስ” ተብሎም ተተርጉሟል።—1 ጴጥሮስ 1:18
-