-
አምላክ ኃጢአታችንን እንድንናዘዝ ይጠብቅብናል?መጠበቂያ ግንብ—2010 | መስከረም 1
-
-
አሁንም ወደ ያዕቆብ መጽሐፍ ስንመለስ የሚከተሉትን አበረታች ቃላት እናገኛለን፦ “ከእናንተ መካከል [በመንፈሳዊ] የታመመ ሰው አለ? የጉባኤ ሽማግሌዎችን ወደ እሱ ይጥራ፤ እነሱም በይሖዋ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፤ ይሖዋም ያስነሳዋል። በተጨማሪም ኃጢአት ሠርቶ ከሆነ ይቅር ይባልለታል።”—ያዕቆብ 5:14, 15
-
-
አምላክ ኃጢአታችንን እንድንናዘዝ ይጠብቅብናል?መጠበቂያ ግንብ—2010 | መስከረም 1
-
-
በመጀመሪያ ‘ዘይት መቀባት’ ያስፈልጋቸዋል። ይህ የአምላክ ቃል ያለውን የመፈወስ ኃይል ያመለክታል። ሐዋርያው ጳውሎስ “የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ ነው፤ . . . የልብንም ሐሳብና ዓላማ መረዳት ይችላል” በማለት ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ አድርጎታል። (ዕብራውያን 4:12) ሽማግሌዎች መጽሐፍ ቅዱስን በጥሩ ሁኔታ በመጠቀም በመንፈሳዊ የታመመው ሰው የችግሩን መንስኤ እንዲያስተውልና በአምላክ ፊት ያለውን አቋም ለማስተካከል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን እንዲወስድ ሊረዱት ይችላሉ።
-