የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክ ኃጢአታችንን እንድንናዘዝ ይጠብቅብናል?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መስከረም 1
    • አሁንም ወደ ያዕቆብ መጽሐፍ ስንመለስ የሚከተሉትን አበረታች ቃላት እናገኛለን፦ “ከእናንተ መካከል [በመንፈሳዊ] የታመመ ሰው አለ? የጉባኤ ሽማግሌዎችን ወደ እሱ ይጥራ፤ እነሱም በይሖዋ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፤ ይሖዋም ያስነሳዋል። በተጨማሪም ኃጢአት ሠርቶ ከሆነ ይቅር ይባልለታል።”—ያዕቆብ 5:14, 15

      እዚህም ላይ መንጋው የሚያስፈልገውን ለሟሟላት ሽማግሌዎች እርምጃ እንደሚወስዱ ተገልጿል። ይህን የሚያደርጉት እንዴት ነው? ግለሰቡ ኃጢአቱን ሲናዘዝ መስማት ብቻ በቂ ሊሆን አይችልም። ይህ ሰው መንፈሳዊ ሕመም ስላለበት ‘እንዲፈወስ’ ሽማግሌዎች ሊያደርጓቸው የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ነገሮች አሉ። ያዕቆብ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ሁለት ነገሮችን ጠቅሷል።

  • አምላክ ኃጢአታችንን እንድንናዘዝ ይጠብቅብናል?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መስከረም 1
    • ቀጥሎም “በእምነት የቀረበ ጸሎት” ያስፈልጋል። ሽማግሌዎቹ የሚያቀርቡት ጸሎት አምላክ ፍትሕን የሚያስፈጽምበትን መንገድ ባያስለውጠውም በክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ኃጢአትን ይቅር ለማለት ዝግጁ በሆነው አምላክ ፊት ጸሎታቸው ትልቅ ቦታ አለው። (1 ዮሐንስ 2:2) አምላክ ከልቡ ንስሐ የገባና “ለንስሐ የሚገባ ሥራ” የሚሠራ ማንኛውንም ኃጢአተኛ ለመርዳት ዝግጁ ነው።—የሐዋርያት ሥራ 26:20

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ