የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ፈተናዎች እየደረሱባችሁም ደስታችሁን ጠብቃችሁ መኖር የምትችሉት እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021 | የካቲት
    • 2 ማንም ሰው ቢሆን ስደት ደስታ ያስገኛል ብሎ ላያስብ ይችላል። የአምላክ ቃል ግን ስለ ስደት እንዲህ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረን ይነግረናል። ለምሳሌ ያህል፣ ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ ፈተና ሲደርስብን በጭንቀት ከመዋጥ ይልቅ እንደ ደስታ እንድንቆጥረው ነግሮናል። (ያዕ. 1:2, 12) ኢየሱስም ቢሆን ስደት ሲደርስብን ልንደሰት እንደሚገባ ተናግሯል። (ማቴዎስ 5:11⁠ን አንብብ።) ታዲያ ፈተናዎች እየደረሱብንም ደስታችንን ጠብቀን መቀጠል የምንችለው እንዴት ነው? ያዕቆብ ለጥንቶቹ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ የሚገኙ አንዳንድ ሐሳቦችን በመመርመር ብዙ ትምህርት ማግኘት እንችላለን። በቅድሚያ በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያኖች የገጠሟቸውን አንዳንድ ፈተናዎች እንመልከት።

      በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ምን ፈተናዎች አጋጥመዋቸዋል?

      3. ያዕቆብ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ከሆነ ብዙም ሳይቆይ ምን ተከሰተ?

      3 የኢየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ ደቀ መዝሙር ከሆነ ብዙም ሳይቆይ በኢየሩሳሌም ባሉ ክርስቲያኖች ላይ ተቃውሞ ተነሳ። (ሥራ 1:14፤ 5:17, 18) ደቀ መዝሙሩ እስጢፋኖስ ሲገደል ደግሞ ብዙ ክርስቲያኖች ከተማዋን ጥለው በመውጣት “በይሁዳና በሰማርያ ክልሎች ሁሉ ተበተኑ”፤ እንዲያውም አንዳንዶቹ እስከ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ርቀው ሄደዋል። (ሥራ 7:58–8:1፤ 11:19) እነዚህ ደቀ መዛሙርት ምን ያህል ከባድ ሁኔታ እንደገጠማቸው መገመት እንችላለን። ያም ቢሆን ምሥራቹን በሄዱበት ሁሉ በቅንዓት ሰብከዋል፤ እንዲሁም በመላው የሮም ግዛት ጉባኤዎች ተቋቁመዋል። (1 ጴጥ. 1:1) ሆኖም እነዚህ ክርስቲያኖች ከዚህም የከፉ ፈተናዎች ይጠብቋቸው ነበር።

      4. የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ምን ሌሎች ፈተናዎች ነበሩባቸው?

      4 የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ልዩ ልዩ ፈተናዎች አጋጥመዋቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በ50 ዓ.ም. ገደማ የሮም ንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ አይሁዳውያን ሁሉ ሮምን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ። ስለዚህ ክርስቲያን የሆኑ አይሁዳውያን ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ሌላ አካባቢ ለመሰደድ ተገደዱ። (ሥራ 18:1-3) በ61 ዓ.ም. ገደማ ሐዋርያው ጳውሎስ የእምነት ባልንጀሮቹ በአደባባይ እንደተነቀፉ፣ እንደታሰሩና እንደተዘረፉ ጽፎ ነበር። (ዕብ. 10:32-34) እንደ ማንኛውም ሰው ሁሉ ደግሞ እነዚያ ክርስቲያኖች ከድህነት ወይም ከህመም ጋር መታገል ነበረባቸው።—ሮም 15:26፤ ፊልጵ. 2:25-27

  • ፈተናዎች እየደረሱባችሁም ደስታችሁን ጠብቃችሁ መኖር የምትችሉት እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021 | የካቲት
    • ፎቶግራፎች፦ 1. የፋኖስ መብራት ነፋስና ዝናብ ቢኖርም ብርሃን መስጠቱን ይቀጥላል። 2. በዕድሜ የገፋ አንድ ወንድም የተከፈተ መጽሐፍ ቅዱስ በእጁ ይዞ።

      የፋኖስ ብርሃን መከለያ ስላለው በቀላሉ እንደማይጠፋ ሁሉ ይሖዋ የሚሰጠን ጥልቅ ደስታም ከልባችን አይጠፋም (አንቀጽ 6⁠ን ተመልከት)

      6. በሉቃስ 6:22, 23 መሠረት አንድ ክርስቲያን ፈተናዎች እየደረሱበትም ደስተኛ የሚሆነው ለምንድን ነው?

      6 ሰዎች ደስተኛ የሚሆኑት ጥሩ ጤና፣ ብዙ ገንዘብ ወይም ሰላማዊ የቤተሰብ ሕይወት ሲኖራቸው እንደሆነ ሊሰማቸው ይችላል። ያዕቆብ የጻፈው ግን የአምላክ መንፈስ ፍሬ ገጽታ ስለሆነው ደስታ ሲሆን ይህ ደስታ ግለሰቡ ባለበት ሁኔታ ላይ የተመካ አይደለም። (ገላ. 5:22) ለአንድ ክርስቲያን ደስታ ወይም ጥልቅ እርካታ የሚያስገኝለት ይሖዋን እያስደሰተና የኢየሱስን ምሳሌ እየተከተለ እንዳለ ማወቁ ነው። (ሉቃስ 6:22, 23⁠ን አንብብ፤ ቆላ. 1:10, 11) በአንድ ክርስቲያን ልብ ውስጥ ያለው ደስታ ከፋኖስ ብርሃን ጋር ሊመሳሰል ይችላል፤ የፋኖስ ብርሃን መከለያ ስላለው በቀላሉ አይጠፋም። በተመሳሳይም አንድ ክርስቲያን ጤንነቱ ቢቃወስ ወይም ገንዘብ ቢያጣም እንኳ ውስጣዊ ደስታው አይጠፋም። ከቤተሰቡ አባላት ወይም ከሌሎች የሚደርስበት ፌዝና ተቃውሞም ደስታውን አያጨልመውም። ተቃዋሚዎች ደስታውን ለማጥፋት የሚያደርጉት ጥረት ደስታውን አያደበዝዘውም፤ እንዲያውም ይበልጥ ደምቆ እንዲበራ ያደርገዋል። በእምነታችን ምክንያት የሚደርሱብን ፈተናዎች እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደሆንን ያረጋግጣሉ። (ማቴ. 10:22፤ 24:9፤ ዮሐ. 15:20) ያዕቆብ “ወንድሞቼ ሆይ፣ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት” ብሎ የጻፈው በዚህ የተነሳ ነው።—ያዕ. 1:2

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ