የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ለባለ ትዳሮች የሚሆን ጥበብ ያዘለ መመሪያ
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | መጋቢት 1
    • 15, 16. አማኝ ያልሆነ አንድ ባል ክርስቲያን ሚስቱ የምታሳየው የትኛው ባሕርይ ሊማርከው ይችላል?

      15 አንድን ባል ሊማርከው የሚችለው ምን ዓይነት ባሕርይ ነው? ክርስቲያን ሴቶች እንዲያዳብሩ የሚጠበቅባቸው ባሕርይ እንደሆነ የታወቀ ነው። ጴጥሮስ እንዲህ ብሏል:- “ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤ ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን። ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች ራሳቸውን ያስዋቡት በዚህ ዐይነት ለባሎቻቸው በመገዛት ነበርና። ሣራም አብርሃምን ‘ጌታዬ’ እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም ምንም ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ።”—1 ጴጥሮስ 3:3-6

  • ለባለ ትዳሮች የሚሆን ጥበብ ያዘለ መመሪያ
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | መጋቢት 1
    • 17. ሣራ ለክርስቲያን ሚስቶች ግሩም ምሳሌ የሆነችው እንዴት ነው?

      17 ሣራ ባሎቻቸው አማኝም ሆኑ አልሆኑ ለክርስቲያን ሚስቶች ምሳሌ ተደርጋ የተጠቀሰች ሴት ናት። ሣራ ምንም ሳታንገራግር አብርሃም ራሷ መሆኑን ተቀብላለች። በልቧ እንኳ ሳይቀር ‘ጌታዬ’ ብላ ጠርታዋለች። (ዘፍጥረት 18:12) ይህ ግን ክብሯን አልቀነሰባትም። በይሖዋ ላይ ጽኑ እምነት የነበራት በመንፈሳዊ ጠንካራ ሴት እንደሆነች ግልጽ ነው። በእርግጥም ‘በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንድንሮጥ’ ሊያነሳሱን ከሚችሉ ‘እንደ ደመና ካሉ ብዙ ምስክሮች’ መካከል አንዷ ናት። (ዕብራውያን 11:11፤ 12:1) አንዲት ክርስቲያን ሚስት የሣራን አርዓያ መከተሏ ክብሯን አይቀንስባትም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ