የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በጣም አዘነላቸው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • አንዲት እህት ሌላ እህትን ስታጽናና።

      “የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ”

      7. ራስን በሌሎች ቦታ ማስቀመጥን ለመማር ምን ሊረዳን ይችላል? ይህ ባሕርይ በምን ይገለጻል?

      7 ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ራሳችንን በሌሎች ቦታ በማስቀመጥ ረገድ የኢየሱስን ምሳሌ መከተል ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስ “የሌላውን ስሜት የምትረዱ ሁኑ” የሚል ማበረታቻ ይሰጠናል።b (1 ጴጥሮስ 3:8) ከባድ በሽታ ወይም የመንፈስ ጭንቀት የሚያሠቃየውን ሰው ስሜት ሙሉ በሙሉ መረዳት ቀላል ላይሆንልን ይችላል፤ በተለይ እንደ እነሱ ያለ ሕመም አጋጥሞን የማያውቅ ከሆነ። ይሁንና ራስን በሌሎች ቦታ ማስቀመጥ የግድ በዚያ ሁኔታ ማለፍን እንደማይጠይቅ አስታውስ። ኢየሱስ ታሞ ባያውቅም የታማሚው ሰው ሥቃይ ይሰማው ነበር። እኛስ እንዲህ ያለ ባሕርይ ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው? መከራ የደረሰባቸው ሰዎች የልባቸውን ግልጥልጥ አድርገው ሲነግሩንና ስሜታቸውን ሲገልጹልን በትዕግሥት በማዳመጥ ነው። ‘እኔ በእሱ ወይም በእሷ ቦታ ብሆን ኖሮ ምን ይሰማኝ ነበር?’ እያልን ራሳችንን ልንጠይቅ እንችላለን። (1 ቆሮንቶስ 12:​26) የሌሎች ስሜት በጥልቅ የሚሰማን ዓይነት ሰዎች ለመሆን ጥረት ካደረግን “የተጨነቁትን” በተሻለ ሁኔታ ‘ማጽናናት’ እንችላለን። (1 ተሰሎንቄ 5:​14) አንዳንድ ጊዜ የሌሎችን ስሜት መረዳታችን የሚገለጸው በቃል ብቻ ሳይሆን በእንባም ሊሆን ይችላል። ሮም 12:​15 “ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ” ይላል።

  • “በጣም አዘነላቸው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • b ‘የሌላውን ስሜት መረዳት’ ተብሎ የተተረጎመው ግሪክኛ ቅጽል በቀጥታ ሲተረጎም “አብሮ መሠቃየት” ማለት ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ