የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን!
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ሰኔ 15
    • “የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ”

      ሐዋርያው ጴጥሮስ ክርስቲያኖች “በብዙ ዐይነት ፈተና . . . መከራን” እንደሚቀበሉ ተናግሯል። (1 ጴጥሮስ 1:6) ቆየት ብሎም በመንፈስ አነሳሽነት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ስለ “እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ” ገልጿል። (1 ጴጥሮስ 4:10) “ልዩ ልዩ” ለሚለው ሐረግ የገባው የመጀመሪያው የግሪክኛ ቃል ቀደም ሲል በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርሰው መከራ ከተገለጸበት ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር ይህን ቃል አስመልክተው ሐሳብ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል:- “ይህ ድንቅ ሐሳብ ነው። . . . የአምላክ ጸጋ ፓይኪሎስ እንደሆነ መገለጹ ይህ ጸጋ ሊያሸንፈው የማይችል ምንም ዓይነት ሰብዓዊ ሁኔታ አለመኖሩን የሚያሳይ ነው።” አክለውም እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል:- “የአምላክ ጸጋ መፍትሄ የማያገኝለትና የማያሸንፈው ምንም ዓይነት ሁኔታ፣ ችግር እንዲሁም ድንገተኛ ወይም አጣዳፊ ክስተት የለም። በሕይወት ውስጥ የአምላክ ጸጋ የማይቋቋመው ምንም ነገር የለም። ይህ ገላጭ የሆነ ፓይኪሎስ የተባለ ቃል የአምላክ ጸጋ ብዙ ገጽታ ያለው እንደሆነና ሁሉንም ዓይነት ችግሮች እንድንቋቋም እንደሚረዳን ያስታውሰናል።”

      የአምላክ ጸጋ ፈተናዎችን ለመቋቋም ይረዳናል

      ጴጥሮስ በተናገረው መሠረት የአምላክ ጸጋ የሚገለጥበት አንዱ መንገድ በተለያዩ የክርስቲያን ጉባኤ አባላት አማካኝነት ነው። (1 ጴጥሮስ 4:11) እያንዳንዱ የአምላክ አገልጋይ በአሁኑ ጊዜ ፈተና እያጋጠማቸው ላሉ ክርስቲያኖች የብርታት ምንጭ ሆኖ ለማገልገል የሚያስችል መንፈሳዊ ስጦታ ወይም ችሎታ አለው። (ሮሜ 12:6-8) ለምሳሌ አንዳንድ የጉባኤው አባላት የተዋጣላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ናቸው። ማስተዋል የተሞላበት ንግግራቸው ሌሎች እንዲበረታቱና እንዲጸኑ ይረዳቸዋል። (ነህምያ 8:1-4, 8, 12) ሌሎች ደግሞ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን አዘውትረው ቤታቸው እየሄዱ እረኝነት ያደርጉላቸዋል። እንደነዚህ የመሰሉት ጉብኝቶች ለማበረታታትና ‘ልብን ለማጽናናት’ የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ናቸው። (ቈላስይስ 2:2) የበላይ ተመልካቾች እንደዚህ የመሰሉ እምነት የሚያጠናክሩ ጉብኝቶችን ሲያደርጉ መንፈሳዊ ስጦታን ያካፍላሉ። (ዮሐንስ 21:16) በጉባኤ የሚገኙ ሌሎችም በፈተናዎች ላዘኑት የእምነት አጋሮቻቸው ሞቅ ያለ ፍቅር፣ ርኅራኄና አሳቢነት በማሳየት የታወቁ ናቸው። (የሐዋርያት ሥራ 4:36፤ ሮሜ 12:10፤ ቈላስይስ 3:10) እንደነዚህ የመሳሰሉት አፍቃሪ ወንድሞችና እህቶች የሚያሳዩት ርኅራኄና የሚያደርጉት እርዳታ የአምላክ ጸጋ የሚገለጽበት መንገድ ነው።—ምሳሌ 12:25፤ 17:17

  • ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን!
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ሰኔ 15
    • በእርግጥም የደረሰብን ፈተና ምንም ዓይነት “መልክ” ቢኖረው የአምላክ ጸጋ እንድንቋቋመው ያስችለናል። (ያዕቆብ 1:17) የይሖዋ አገልጋዮች የሚደርሱባቸው ፈተናዎችና አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተለያዩ ቢሆኑም አምላክ በወቅቱ የሚሰጣቸው አስፈላጊ የሆነ እርዳታ “ብዙ ገጽታ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ” አንዱ መግለጫ ነው። (ኤፌሶን 3:10) በዚህ አባባል አትስማማም?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ