-
‘ታማኙ ባሪያ’ ፈተናውን አለፈ!መጠበቂያ ግንብ—2004 | መጋቢት 1
-
-
15, 16. (ሀ) ጌታው ከባሪያዎቹ ጋር ሒሳብ የተሳሰበው መቼ ነው? (ለ) ታማኝ ሆነው ለተገኙት ባሪያዎች ‘በንግዱ’ ሥራ ምን ተጨማሪ ኃላፊነቶች ተሰጣቸው?
15 ምሳሌው ሲቀጥል እንዲህ ይላል፦ “ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቈጣጠራቸው።” (ማቴዎስ 25:19 የ1954 ትርጉም) ኢየሱስ በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ካረገ ከረጅም ጊዜ በኋላ ማለትም በ1914 ንጉሣዊ ሥልጣኑን ያዘ። ከዚያም ሦስት ዓመት ተኩል ካለፈ በኋላ በ1918 “ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ደርሶአልና” በሚሉት የጴጥሮስ ቃላት ፍጻሜ መሠረት ወደ አምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ መጣ። (1 ጴጥሮስ 4:17፤ ሚልክያስ 3:1) አዎን፣ ከባሪያዎቹ ጋር ሒሳብ የሚተሳሰብበት ጊዜ ደርሶ ነበር።
-
-
‘ታማኙ ባሪያ’ ፈተናውን አለፈ!መጠበቂያ ግንብ—2004 | መጋቢት 1
-
-
በማቴዎስ 24 እና 25 ላይ ኢየሱስ በተለያየ መንገድ ‘እንደሚመጣ’ ተነግሯል። መምጣት ሲባል ግን የግድ በአካል መገኘትን አያመለክትም። ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ ትኩረቱን ወደ ሰው ልጆች ወይም ወደ ተከታዮቹ ያደርጋል ማለት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የሚመጣው ለፍርድ ነው። በመሆኑም በ1914 በንጉሣዊ ሥልጣኑ ላይ ተቀምጦ ለመግዛት ‘መጣ።’ (ማቴዎስ 16:28፤ 17:1፤ የሐዋርያት ሥራ 1:11) በ1918 ይሖዋን እናገለግላለን በሚሉ ሰዎች ላይ ለመፍረድ የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ ሆኖ ‘መጣ።’ (ሚልክያስ 3:1-3፤ 1 ጴጥሮስ 4:17) በአርማጌዶን ደግሞ በይሖዋ ጠላቶች ላይ የቅጣት ፍርድ ለማስፈጸም ‘ይመጣል።’—ራእይ 19:11-16
-