-
ለሌሎች አሳቢ በመሆን ረገድ ይሖዋን እየኮረጅክ ነው?መጠበቂያ ግንብ—2007 | ሰኔ 15
-
-
የይሖዋ ፍቅራዊ አሳቢነት በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥም ተንጸባርቋል። ኢየሱስ ክርስቶስ የጉባኤው ራስ እንደመሆኑ መጠን ሽማግሌዎች ለመንጋው አሳቢ እንዲሆኑ መመሪያ ሰጥቷቸዋል። (ዮሐንስ 21:15-17) የበላይ ተመልካች ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ልብ ብሎ መጠበቅ” የሚል ትርጉም ካለው ግስ ጋር ተዛማጅነት አለው። ጴጥሮስ ይህ እንዴት መከናወን እንደሚኖርበት ጎላ አድርጎ ሲጠቅስ ለሽማግሌዎች የሚከተለውን መመሪያ ሰጥቷል:- “በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቁትም ከእግዚአብሔር እንደሚጠበቅባችሁ በግድ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ጽኑ ፍላጎት ይሁን፤ እንዲሁም በዐደራ ለተሰጣችሁ መንጋ መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በላያቸው በመሠልጠን አይሁን።”—1 ጴጥሮስ 5:2, 3
-
-
ለሌሎች አሳቢ በመሆን ረገድ ይሖዋን እየኮረጅክ ነው?መጠበቂያ ግንብ—2007 | ሰኔ 15
-
-
ይሁን እንጂ ከላይ የተጠቀሱት የጴጥሮስ ቃላት አንድ አደጋ እንዳለ ይጠቁማሉ፤ ይኸውም ሽማግሌዎች በጉባኤው ላይ ‘ከመሠልጠን’ መቆጠብ እንደሚኖርባቸው ያስጠነቅቃቸዋል። አንድ ሽማግሌ አላስፈላጊ ሕጎችን ሊያወጣ ይችላል፤ ይህ ደግሞ በመንጋው ላይ ‘እየሠለጠነ’ እንዳለ ከሚጠቁሙት ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። አንድ ሽማግሌ መንጋውን የመጠበቅ ግዴታውን በጣም አክብዶ ከመመልከቱ የተነሳ ከገደብ አልፎ አንዳንድ ነገሮችን ያደርግ ይሆናል። በሩቅ ምሥራቅ አገሮች በሚገኝ አንድ ጉባኤ ውስጥ ሽማግሌዎች በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ሌሎችን ሰላም ማለት የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ ሕጎችን አውጥተው የነበረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መጀመሪያ ማን መናገር እንደሚኖርበትና የመሳሰሉት ይገኙበታል። ሽማግሌዎቹ ይህን ያደረጉት እነዚህን ሕጎች መከተል ለጉባኤው ሰላም አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ስለተሰማቸው ነው። ሽማግሌዎቹ ይህን ሕግ ያወጡት ከጥሩ ዓላማ ተነሳስተው መሆኑ ባያጠያይቅም ይሖዋ ሕዝቡን የሚይዝበትን መንገድ ኮርጀዋል ሊባል ይችላል? ሐዋርያው ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ የነበረው አመለካከት በተናገራቸው ቃላት በግልጽ ተንጸባርቋል። ጳውሎስ “ጸንታችሁ የምትቆሙት በእምነት ስለ ሆነ፣ ደስ እንዲላችሁ ከእናንተ ጋር እንሠራለን እንጂ በእምነታችሁ ላይ ለመሠልጠን አይደለም” ብሏል። (2 ቆሮንቶስ 1:24) ይሖዋ በሕዝቦቹ ላይ እምነት ይጥላል።
-