-
ራሴን የማጥፋት ሐሳብ ሲመጣብኝ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳኝ ይችላል?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ [በአምላክ] ላይ ጣሉ፤ ምክንያቱም እሱ ስለ እናንተ ያስባል።”—1 ጴጥሮስ 5:7
የጥቅሱ ትርጉም፦ አምላክ ያስጨነቀህን ማንኛውንም ነገር ምንም ሳትሸሽግ በግልጽ እንድትነግረው ግብዣ አቅርቦልሃል።
አምላክ ውስጣዊ ሰላም እንድታገኝና ሁኔታህን መቋቋም የምትችልበት አቅም እንዲኖርህ ሊረዳህ ይችላል። (ፊልጵስዩስ 4:6, 7, 13) በዚህ መንገድ፣ በቅን ልቦና ተነሳስተው የእሱን እርዳታ የሚጠይቁ ሰዎችን ይደግፋቸዋል።—መዝሙር 55:22
-