-
ቀጰዶቅያ—በነፋስና በውኃ በተቀረጹ ዋሻዎች ውስጥ መኖርመጠበቂያ ግንብ—2004 | ሐምሌ 15
-
-
ሐዋርያው ጴጥሮስ በመንፈስ አነሳሽነት በጻፈው የመጀመሪያው ደብዳቤ ላይ ቀጰዶቅያን ጠቅሷል። ደብዳቤውን ከላከላቸው ሰዎች መካከል “በቀጰዶቅያ፣ . . . ተበትነው በመጻተኝነት” የሚኖሩ ክርስቲያኖች ይገኙበት ነበር። (1 ጴጥሮስ 1:1) ቀጰዶቅያ ምን ዓይነት ቦታ ነበር? ነዋሪዎቹስ ከድንጋይ በተወቀሩ ዋሻዎች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው? ከክርስትና ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁት እንዴት ነበር?
-
-
ቀጰዶቅያ—በነፋስና በውኃ በተቀረጹ ዋሻዎች ውስጥ መኖርመጠበቂያ ግንብ—2004 | ሐምሌ 15
-
-
በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በቀጰዶቅያ የሚኖሩ አይሁዳውያን ነበሩ። በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከዚህ አካባቢ የመጡ አይሁዳውያን የጰንጠቆስጤን በዓል ለማክበር በኢየሩሳሌም ተገኝተው ነበር። በመሆኑም መንፈስ ቅዱስ ከፈሰሰ በኋላ ሐዋርያው ጴጥሮስ የሰጠውን ምሥክርነት ከቀጰዶቅያ የመጡ አይሁዳውያንም አዳምጠው ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 2:1-9) ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ ለመልእክቱ ምላሽ ሰጥተው አዲሱን እምነታቸውን ይዘው ወደ አገራቸው ሳይሄዱ አይቀርም። በመሆኑም ጴጥሮስ በመጀመሪያው ደብዳቤው ላይ የቀጰዶቅያ ክርስቲያኖችን ሊጠቅስ ችሏል።
-