የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 2—ዘጸአት
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 5
    • 30 የዘጸአት መጽሐፍ የመንፈሳዊ እስራኤል ክርስቲያናዊ ብሔር ክብራማ ነፃነቱን የሚጎናጸፍበትን ጊዜ በማመልከት የይሖዋን ስምና ሉዓላዊነቱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሲሆን ስለዚሁ ብሔር እንዲህ ብሏል:- “ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትነግሩ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ።” ይሖዋ ስሙን ለማስከበር ሲል መንፈሳዊ እስራኤል የሚሆኑትን ከዓለም በመሰብሰብ ያሳየው ኃይል ከጥንቷ ግብጽ ሕዝቡን ለማውጣት ካሳየው ተአምራዊ ኃይል ምንም አይተናነስም። ይሖዋ ፈርዖንን በሕይወት አቆይቶ ኃይሉ እንዲገለጥበትና ስሙ እንዲታወቅ በማድረግ ወደፊት በክርስቲያን ምሥክሮቹ አማካኝነት የሚከናወን እጅግ ታላቅ የምሥክርነት ሥራ እንደሚኖር አመልክቷል።—1 ጴጥ. 2:9, 10፤ ሮሜ 9:17፤ ራእይ 12:17

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 60—1 ጴጥሮስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 17
    • 13 ጴጥሮስ አስፈሪ ችግሮችና ስደቶች ብቅ ብቅ ማለት በጀመሩበት ጊዜ ጥንካሬ የሚጨምር ማበረታቻ ሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ መልእክቱ ዛሬም ቢሆን ተመሳሳይ ፈተና ለሚያጋጥማቸው ሁሉ ይህ ነው የማይባል ጠቃሚ ምክር ይዟል። ጴጥሮስ የይሖዋን ቃል በሚጠቅስበት ጊዜ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዴት እንደተጠቀመባቸው ልብ በል:- “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።” (1 ጴጥ. 1:16፤ ዘሌ. 11:44) ከዚያም፣ በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፉት ከሌሎቹ ቅዱሳን መጻሕፍት በብዛት በጠቀሰበት ምዕራፍ ውስጥ የክርስቲያን ጉባኤ በክርስቶስ መሠረት ላይ በሕያዋን ድንጋዮች የተገነባ መንፈሳዊ ቤት የሆነበትን መንገድ አስረድቷል። ይህን ያደረገበት ዓላማ ምን ነበር? ጴጥሮስ እንዲህ በማለት መልሱን ይሰጣል:- “ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ለራሱ የለያችሁ ሕዝብ ናችሁ።” (1 ጴጥ. 2:4-10፤ ኢሳ. 28:16፤ መዝ. 118:22፤ ኢሳ. 8:14፤ ዘፀ. 19:5, 6፤ ኢሳ. 43:21፤ ሆሴዕ 1:10፤ 2:23) ጴጥሮስ ‘የማይጠፋ፣ የማይበላሽና የማይለወጥ ርስት፣’ ‘የማይጠፋ አክሊል’ እንዲሁም ‘በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የመጠራትን’ የመንግሥቱን ተስፋ እንደሚያገኝ የተናገረለት ‘የንጉሥ ካህናት፣’ የአምላክ ቅዱስ ብሔር የሆነው የካህናት ቡድን ነው። እነሱም ‘ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታቸው ታላቅ እንዲሆን’ መደሰታቸውን እንዲቀጥሉ ከፍተኛ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል።—1 ጴጥ. 1:4፤ 5:4, 10፤ 4:13

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ