የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እምነት በማሳየት አምላክ ለሰጠን ተስፋዎች አዎንታዊ ምላሽ ስጥ
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | ሐምሌ 15
    • 4. በእምነታችን ላይ የትኞቹን ባሕርያት መጨመር አለብን?

      4 ይሖዋ በገባልን ተስፋዎች ላይ ያለን እምነትና ከአምላክ ለተሰጠን ነፃነት አመስጋኞች መሆናችን የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ጥሩ ምሳሌ የምናሳይ ክርስቲያኖች እንድንሆን ሊገፋፋን ይገባል። ጴጥሮስ እንዲህ አለ:- “ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፣ በበጎነትም እውቀትን፣ በእውቀትም ራስን መግዛት፣ ራስንም በመግዛት መጽናትን፣ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል [ለአምላክ ያደሩ መሆንን አዓት]፣ እግዚአብሔርንም በመምሰል [ለአምላክ ያደሩ በመሆንም አዓት] የወንድማማችን መዋደድ፣ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።” (2 ጴጥሮስ 1:​5–7) እንደዚህ በማለት ጴጥሮስ በአእምሮአችን ውስጥ ብንቀርጻቸው የሚጠቅሙንን ነገሮች ዘርዝሮልናል። እነዚህን ባሕርያት ቀረብ ብለን በመመልከት እንመርምራቸው።

  • እምነት በማሳየት አምላክ ለሰጠን ተስፋዎች አዎንታዊ ምላሽ ስጥ
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | ሐምሌ 15
    • 9. (ሀ) ለአምላክ ያደሩ መሆን ምንድን ነው? (ለ) ለአምላክ ያደሩ በመሆናችን ላይ የወንድማማች መዋደድን መጨመር ያለብን ለምንድን ነው? (ሐ) በወንድማማች መዋደዳችን ላይ ፍቅርን መጨመር የምንችለው እንዴት ነው?

      9 በጽናታችን ላይ ለአምላክ ያደሩ መሆንን መጨመር ይኖርብናል። ይህም አክብሮታዊ ፍርሃትን፣ አምልኮንና ይሖዋን ማገልገልን ያመለክታል። ለአምላክ ያደሩ መሆንን ስንሠራበትና ይሖዋ ሕዝቡን እንዴት አድርጎ እንደሚይዝ ስንመለከት እምነታችን ያድጋል። ሆኖም አምላካዊ ባሕርያትን ለማሳየት እንድንችል የወንድማማች መዋደድ እንዲኖረን ያስፈልጋል። እንዲያውም “ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?” (1 ዮሐንስ 4:​20) ልባችን ለሌሎቹ የይሖዋ አገልጋዮች እውነተኛ የሆነ የመውደድ ስሜት እንድናሳድርና በማንኛውም ጊዜ የሚበጃቸውን እንድናስብላቸው ሊገፋፋን ይገባል። (ያዕቆብ 2:​14–17) ታዲያ በወንድማማች መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ የተባልነው ለምንድን ነው? ጴጥሮስ እዚህ ላይ ለወንድሞቻችን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የሰው ልጆች ፍቅርን ማሳየት እንደሚኖርብን መናገሩ ግልጽ ነው። ይህ ፍቅር በተለይ ምሥራቹን በመስበክና ሰዎችን በመንፈሳዊ በመርዳት ይገለጻል። — ማቴዎስ 24:​14፤ 28:​19, 20

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ