-
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነውለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ የአምላክ ቃል ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት 40 የሚሆኑ ሰዎች ናቸው፤ የተጻፈውም ከ1513 ዓ.ዓ. እስከ 98 ዓ.ም. ድረስ ባሉት 1,600 ዓመታት ገደማ ውስጥ ነው። ጸሐፊዎቹ የተለያየ አስተዳደግና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ናቸው። ያም ቢሆን ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እርስ በርስ ይስማማሉ። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ስለሆነ ነው። (1 ተሰሎንቄ 2:13ን አንብብ።) ጸሐፊዎቹ የመዘገቡት የራሳቸውን ሐሳብ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ‘ከአምላክ የተቀበሉትን በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው ተናግረዋል።’a (2 ጴጥሮስ 1:21) አምላክ ሰዎች የእሱን ሐሳብ እንዲጽፉ ለመምራት ወይም ለማነሳሳት መንፈስ ቅዱስን ተጠቅሟል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16
-
-
ይሖዋ ምን ዓይነት አምላክ ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. መንፈስ ቅዱስ—አምላክ የተለያዩ ሥራዎችን ለማከናወን የሚጠቀምበት ኃይል
የተለያዩ ሥራዎችን ለማከናወን እጃችንን እንደምንጠቀም ሁሉ ይሖዋም ቅዱስ መንፈሱን ይጠቀማል። መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አካል ሳይሆን አምላክ የተለያዩ ነገሮችን ለማከናወን የሚጠቀምበት ኃይል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ሉቃስ 11:13ን እና የሐዋርያት ሥራ 2:17ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
አምላክ፣ ቅዱስ መንፈሱን ለማግኘት በሚጠይቁት ሰዎች ላይ ይህን መንፈስ ‘ያፈስሳል።’ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ አካል ነው ወይስ አምላክ የተለያዩ ነገሮችን ለማከናወን የሚጠቀምበት ኃይል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
ይሖዋ አስደናቂ ነገሮችን ለማከናወን ቅዱስ መንፈሱን ይጠቀማል። መዝሙር 104:30ን እና 2 ጴጥሮስ 1:20, 21ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ መንፈስ ቅዱስን የተጠቀመባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
-