የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልህ ነገር አድናቆት እንዳለህ አሳይ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 3. አድናቆት ለተግባር ያነሳሳል

      ውኃ ውስጥ ልትሰጥም ስትል አንድ ሰው አዳነህ እንበል። ይህ ሰው ያደረገልህን ነገር ትረሳዋለህ? ወይስ ላደረገልህ ነገር አድናቆትህን ለመግለጽ ትሞክራለህ?

      የዘላለም ሕይወት የማግኘት አጋጣሚ የተከፈተልን በይሖዋ ደግነት ነው። አንደኛ ዮሐንስ 4:8-10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • የኢየሱስ መሥዋዕት ልዩ ስጦታ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

      • ይሖዋና ኢየሱስ ስላደረጉልህ ነገር ምን ይሰማሃል?

      ይሖዋና ኢየሱስ ላደረጉልን ነገር አድናቆታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ሁለተኛ ቆሮንቶስ 5:15⁠ን እንዲሁም 1 ዮሐንስ 4:11⁠ን እና 5:3⁠ን አንብቡ። እያንዳንዱን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በዚህ ጥቅስ መሠረት አድናቆታችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ራስህን ለይሖዋ መወሰንና መጠመቅ ያለብህ ለምንድን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 1. አንድ ሰው ራሱን ለይሖዋ ለመወሰን እንዲነሳሳ የሚያደርገው ምንድን ነው?

      ራሳችንን ለይሖዋ ለመወሰን የሚያነሳሳን ፍቅር ነው። (1 ዮሐንስ 4:10, 19) መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የሚል ምክር ይሰጠናል፦ “አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ አእምሮህና በሙሉ ኃይልህ ውደድ።” (ማርቆስ 12:30) ለአምላክ ያለንን ፍቅር የምናሳየው በምንናገረው ነገር ብቻ ሳይሆን በምናደርገው ነገር ጭምር ነው። በጣም የሚዋደዱ ጥንዶች ትዳር እንደሚመሠርቱ ሁሉ እኛም ለይሖዋ ያለን ፍቅር ራሳችንን ለእሱ እንድንወስንና እንድንጠመቅ ያነሳሳናል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ