-
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥር 15
-
-
“ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም”
4-6. (ሀ) ‘ከባድ’ ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ጥሬ ፍቺ ምንድን ነው? (ለ) የአምላክ ትእዛዞች ከባዶች አይደሉም የምንለው ለምንድን ነው?
4 “ትእዛዙንም ጠብቅ።” አምላክ ከእኛ የሚፈልገው መሠረታዊ ነገር ይህ ነው። ታዲያ ይህን ከእኛ መጠየቁ የሚበዛበት ነውን? በፍጹም አይደለም። ሐዋርያው ዮሐንስ የአምላክን ትእዛዞች ወይም ብቃቶች በተመለከተ መንፈሳችንን የሚያሳርፍ ነገር ይነግረናል። እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።”— 1 ዮሐንስ 5:3 ፊደላቱን ጋደል አድርገን የጻፍናቸው እኛ ነን።
5 እዚህ ላይ ‘ከባድ’ ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ጥሬ ፍቺው “ለመሸከም የሚከብድ” ማለት ነው። ለመቋቋም ወይም ለማሟላት አስቸጋሪ የሆነን ነገር ሊያመለክት ይችላል። ቃሉ በማቴዎስ 23:4 ላይ ጻፎችና ፈሪሳውያን በሕዝቡ ላይ ጥለዋቸው የነበሩት ሰው ሠራሽ ሕጎችና ወጎች ‘ከባድ ሸክም’ መሆናቸውን ለመግለጽ ተሠርቶበታል። በዕድሜ ገፍቶ የነበረው ሐዋርያው ዮሐንስ ለመናገር የፈለገው ነገር ምን እንደሆነ አስተዋላችሁ? የአምላክ ትእዛዛት ከባድ ሸክሞች አይደሉም። ልንጠብቃቸው የማይቻሉ እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮችም አይደሉም። (ከዘዳግም 30:11 ጋር አወዳድር።) በተቃራኒው ደግሞ አምላክን የምንወድ ከሆነ ብቃቶቹን ማሟላት ያስደስተናል። ለይሖዋ ያለንን ፍቅር በተግባር ለመግለጽ የሚያስችል ግሩም አጋጣሚ ይሰጠናል።
-
-
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥር 15
-
-
12. ስለ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ እውቀት መቅሰም ሸክም እንዳልሆነ እንዴት ማስረዳት ትችላለህ?
12 ስለ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ የሚገልጸውን እንዲህ ያለው እውቀት መቅሰም ከባድ ሸክም ነውን? በፍጹም አይደለም! የአምላክ ስም ይሖዋ እንደሆነ፣ የአምላክ መንግሥት ገነትን በምድር ላይ መልሶ እንደሚያቋቁም፣ የሚወደውን ልጁን ለኃጢአታችን ቤዛ አድርጎ እንደሰጠና ሌሎች በጣም ውድ የሆኑ እውነቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታውቅ እንዴት እንደተሰማህ ታስታውሳለህ? ዓይንህን የሸፈነው ግርዶሽ እንደተነሳና ነገሮችን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥርት አድርገህ ማየት እንደጀመርክ ያህል አልነበረምን? ስለ አምላክ እውቀት መቅሰም የሚያስደስት ነገር ነው እንጂ ከባድ ሸክም አይደለም!— መዝሙር 1:1-3፤ 119:97
-
-
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥር 15
-
-
16. አምላክ ለትክክለኛ ሥነ መግባር ካወጣቸው መስፈርቶች ጋር በሚጣጣም መንገድ መኖርና የአምላክን እውነት መቀበል ሸክም የማይሆነው ለምን እንደሆነ አስረዳ።
16 አምላክ ለትክክለኛ ሥነ ምግባር ያወጣቸውን መስፈርቶች ማሟላትና የአምላክን እውነት መቀበል ከባድ ሸክም ይሆንብናልን? የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ካሰብን ከባድ ሸክም አይሆንብንም። ትዳራችን አንዳችን ለሌላው ታማኝ ባለመሆናችን ምክንያት ከመፍረስ ይልቅ ባልና ሚስት የሚዋደዱበትና እርስ በርስ የሚተማመኑበት ትዳር ይሆናል፣ ቤታችን ልጆች ያልተፈለጉ ሸክሞች ሆነው የሚታዩበት፣ ችላ የሚባሉበትና የማይወደዱበት ከመሆን ይልቅ በወላጆቻቸው እንደሚወደዱና እንደሚፈለጉ ተሰምቷቸው የሚኖሩበት ይሆናል፤ ሰውነታችን በኤድስና በሌሎች የአባለ ዘር በሽታዎች የተጎሳቆለና የበደለኛነት ስሜት የሚሰማን ከመሆን ይልቅ ንጹሕ ሕሊናና ጥሩ ጤንነት ይኖረናል። በእርግጥም ይሖዋ እንድናሟላቸው የሚፈልጋቸው ብቃቶች በሕይወት ለመደሰት የሚያስፈልገንን አንድም ነገር እንድናጣ አያደርጉንም!— ዘዳግም 10:12, 13
-
-
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥር 15
-
-
19. ለሕይወትና ለደም አክብሮት በማሳየታችን እንዴት እንደምንጠቀም ግለጽ።
19 ሕይወትንና ደምን በቅድስና መያዝ ከባድ ሸክም ይሆንብናልን? በጭራሽ አይሆንብንም! እስቲ አስቡት። ትንባሆ ከማጨስ ከሚመጣው የሳንባ ካንሰር ነጻ ሆኖ መኖር ሸክም ነው? በአደገኛ ዕፆች ሱስ የአእምሮና የአካል እስረኛ ከመሆን መገላገል ሸክም ነው? በኤድስ፣ በሄፓታይተስ ወይም ደም በመውሰድ በሚመጡ ሌሎች በሽታዎች ከመለከፍ መዳን ሸክም ነው? እንደነዚህ ያሉትን ጎጂ ልማዶችና ድርጊቶች ማስወገዳችን ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝልን መሆኑ ጥርጥር የለውም።— ኢሳይያስ 48:17
20. አንድ ቤተሰብ አምላክ ለሕይወት ያለውን አመለካከት በመያዙ የተጠቀመው እንዴት ነው?
20 አንድ ተሞክሮ እንመልከት። ከጥቂት ዓመታት በፊት የሦስት ወር ተኩል ነፍሰ ጡር የነበረች አንዲት የይሖዋ ምሥክር አንድ ቀን ምሽት ደም ይፈሳት ጀመር። ወዲያው ወደ ሆስፒታል ትወሰዳለች። ሐኪሙ ከመረመራት በኋላ ከነርሶቹ ለአንዷ ጽንሱን ማውጣት እንደሚኖርባቸው ሲነግራት ሰማች። ይሖዋ ያልተወለደውን ሕፃን ሕይወት እንዴት እንደሚመለከት ታውቅ ስለነበረ “ጽንሱ ገና አልሞተ ከሆነ እንዳታወጡት” ብላ ለዶክተሩ በመናገር ጽንሱን ለማስወረድ የቀረበውን ሐሳብ አጥብቃ ተቃወመች። ከዚያ በኋላም አልፎ አልፎ ደም ይፈሳት የነበረ ቢሆንም ከወራት በኋላ ጤነኛ የሆነ ወንድ ልጅ ከቀኗ በፊት ተገላገለች። ይህ ሕፃን በአሁኑ ጊዜ የ17 ዓመት ወጣት ሆኗል። እንዲህ ስትል ትናገራለች:- “ለልጃችን ይህን ሁሉ ነግረነዋል። ወደ ቆሻሻ መጣያ ባለመወርወሩ ደስተኛ እንደሆነ ይናገራል። በሕይወት ሊኖር የቻለበት ብቸኛ ምክንያት እኛ ይሖዋን የምናገለግል መሆናችን እንደሆነ ያውቃል!” በእርግጥም ይህ ቤተሰብ አምላክ ለሕይወት ያለውን አመለካከት ማክበሩ ከባድ ሸክም አልሆነበትም!
-
-
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥር 15
-
-
23, 24. ይሖዋን ከተደራጁት ሕዝቦቹ ጋር ሆኖ ማገልገል ከባድ ሸክም እንዳልሆነ እንዴት በምሳሌ ማስረዳት እንችላለን?
23 ከእነዚህ የተደራጁ ሕዝቦች ጋር ሆኖ ይሖዋን ማገልገል ከባድ ሸክም ነው? በፍጹም አይደለም! እንዲያውም ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶች የሚገኙበትን ዓለም አቀፋዊ የሆነ ቤተሰብ ፍቅርና ድጋፍ ማግኘት መቻል በጣም ውድ የሆነ መብት ነው። (1 ጴጥሮስ 2:17) ነገሩን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል አደጋ ከደረሰበት መርከብ በሕይወት ተርፋችሁ ሳትሰጥሙ ለመቆየት በመጣጣር ላይ ናችሁ እንበል። በጣም ዝላችሁ ‘በቃ አለቀልኝ’ ብላችሁ ስታስቡ ለድንገተኛ አደጋ በተዘጋጀ ጀልባ ውስጥ ያለ ሰው እጁን ሰድዶ ጎትቶ ያወጣችኋል። አዎን፣ በሕይወት የተረፉ ሌሎች ሰዎችም አሉ! ለድንገተኛ አደጋ በተዘጋጀው ጀልባ ውስጥ ሆናችሁ እንዳይሰጥሙ በመታገል ላይ የሚገኙ ሌሎች ሰዎችን እግረ መንገዳችሁን አየጎተታችሁ በማውጣትና ተራ በተራ በመፈራረቅ ጀልባዋን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለማውጣት ትቀዝፋላችሁ እንበል።
-