የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለመቀየር የተደረጉ ጥረቶች ከሽፈዋል
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 4
      • የሥላሴ መሠረተ ትምህርት፦ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ካለቀ በኋላ 300 ዓመታት እንኳ ሳይሞላ፣ የሥላሴ አማኝ የሆነ አንድ ጸሐፊ በ1 ዮሐንስ 5:7 ላይ ‘አብ፣ ቃልና መንፈስ ቅዱስ ሦስትም አንድም ናቸው’ የሚሉትን ቃላት ጨምሮ ነበር። ይህ ሐሳብ በመጀመሪያው ጽሑፍ ላይ አልነበረም። የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት ብሩስ ሜጽገር እንደገለጹት “ከስድስተኛው መቶ ዘመን ወዲህ ይህ ሐሳብ በጥንታዊው ላቲን እና [በላቲን] ቩልጌት በእጅ በተገለበጡ ጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች ውስጥ በተደጋጋሚ መገኘት ጀመረ።”

  • የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለመቀየር የተደረጉ ጥረቶች ከሽፈዋል
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016 | ቁጥር 4
    • በሁለተኛ ደረጃ፣ በዛሬው ጊዜ ብዛት ያላቸው በእጅ የተገለበጡ ጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች መገኘታቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ስህተት የሆኑ ሐሳቦችን ማስተያየት እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ለምሳሌ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሚጠቀሙበት የላቲን ትርጉም ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሆነ ለብዙ መቶ ዓመታት ሲያስተምሩ ኖረዋል። ሆኖም በ1 ዮሐንስ 5:7 ላይ ቀደም ሲል የተጠቀሰውን የተሳሳተ ሐሳብ አስገብተው ነበር። ይህ ስህተት ከፍተኛ ተቀባይነት ባለው ኪንግ ጄምስ ቨርዥን ውስጥም ጭምር ገብቷል! ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ የተገኙት በእጅ የተገለበጡ ሌሎች ጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎች ምን ነገር አሳይተዋል? ብሩስ ሜጽገር “[በ1 ዮሐንስ 5:7 ላይ] የገባው ሐሳብ ከላቲኑ በስተቀር በሁሉም ጥንታዊ ቅጂዎች (ሲሪያክ፣ ኮፕቲክ፣ አርመንኛ፣ ግዕዝ፣ አረብኛ፣ ስላቮኒክ) ውስጥ አይገኝም” በማለት ጽፈዋል። በዚህም የተነሳ ተሻሽለው የወጡ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን እትሞችና ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሶች ይህን የተሳሳተ ሐሳብ አውጥተውታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ