-
ገለልተኛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
2. ገለልተኛ መሆናችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ልክ እንደ ኢየሱስ ሁሉ እኛም ፖለቲካ ውስጥ አንገባም። ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ ሕዝቡ እሱ የፈጸመውን ተአምር አይተው ሊያነግሡት በሞከሩ ጊዜ ፈቃደኛ አልሆነም። (ዮሐንስ 6:15) ለምን? ምክንያቱም በኋላ ላይ እንደተናገረው ‘መንግሥቱ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም።’ (ዮሐንስ 18:36) እኛም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን ገለልተኛ መሆናችንን በተለያዩ መንገዶች እናሳያለን። ለምሳሌ ያህል፣ በጦርነት አንካፈልም። (ሚክያስ 4:3ን አንብብ።) እንደ ባንዲራ ያሉ ብሔራዊ ዓርማዎችን የምናከብር ቢሆንም ለአምላክ የምንሰጠውን ዓይነት ክብር አንሰጣቸውም። (1 ዮሐንስ 5:21) በተጨማሪም የትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የፓርቲውን ዕጩ አንደግፍም ወይም አንቃወምም። በእነዚህና በሌሎች መንገዶች ለአምላክ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ታማኝ እንደሆንን እናሳያለን።
-
-
ገለልተኛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. በሐሳብም ሆነ በድርጊት ገለልተኛ ሁን
አንደኛ ዮሐንስ 5:21ን አንብቡ። ከዚያም ቪዲዮውን ተመልከቱና በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
በቪዲዮው ላይ አዬንጌ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ላለመሆን እንዲሁም ለባንዲራ ሰላምታ እንደመስጠት ባሉ ብሔራዊ ሥነ ሥርዓቶች ላለመካፈል የወሰነው ለምንድን ነው?
ያደረገው ውሳኔ ትክክል ይመስልሃል?
የገለልተኝነት አቋማችንን ሊፈትኑ የሚችሉ ሌሎች ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
የተለያዩ አገሮች የሚሳተፉበትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ስንመለከት ገለልተኝነታችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ፖለቲከኞች የሚያደርጉት ውሳኔ እኛን የሚነካን በሚሆንበት ጊዜም እንኳ ገለልተኝነታችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?
የዜና ዘገባዎች ወይም አብረውን ጊዜ የሚያሳልፉ ሰዎች በገለልተኝነት አቋማችን ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ?
ክርስቲያኖች በአስተሳሰብም ሆነ በድርጊት ገለልተኝነታቸውን መጠበቅ የሚኖርባቸው በየትኞቹ ሁኔታዎች ሥር ነው?
-