-
ይሖዋ የጢሮስን ትዕቢት ይሽራልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
32. ዮሐንስ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው? ይህንንስ ሥራ ላይ ልናውል የምንችለው እንዴት ነው?
32 ያለንበት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በሕይወታችን ውስጥ አንደኛውን ቦታ መያዝ ያለበት የአምላክ መንግሥት ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ የተናገራቸውን ቃላት ሁል ጊዜ ልናስብባቸው ይገባል:- “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ . . . ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።” (1 ዮሐንስ 2:15, 16) ሕልውናችንን ለመጠበቅ ስንል በዓለም ኢኮኖሚያዊ ዝግጅቶች መጠቀም እንዳለብን አይካድም። (2 ተሰሎንቄ 3:10) ከዚህ አንጻር ‘ዓለምን እንጠቀምበታለን።’ ይሁን እንጂ ‘ሙሉ በሙሉ አንጠቀምበትም።’ (1 ቆሮንቶስ 7:31 NW) ለቁሳዊ ነገሮች ማለትም በዓለም ውስጥ ላሉት ነገሮች ከልክ ያለፈ ፍቅር ካደረብን ለይሖዋ ፍቅር የለንም ማለት ነው። ‘የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮትን እንዲሁም የይታይልኝ ባይነት መንፈስን’ መከታተል የአምላክን ፈቃድ ከመፈጸም ጋር የሚጣጣም ነገር አይደለም።d ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራው ደግሞ የአምላክን ፈቃድ ማድረግ ነው።—1 ዮሐንስ 2:16, 17 NW
-
-
ይሖዋ የጢሮስን ትዕቢት ይሽራልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
d “የይታይልኝ ባይነት መንፈስ” የሚለው መግለጫ አላዞኒያ ከሚለው የግሪክኛ ቃል የተተረጎመ ሲሆን “በምድራዊ ነገሮች ምቾት የሚተማመን ከንቱና ባዶ ትዕቢት” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል።—ዘ ኒው ቴየርስ ግሪክ ኢንግሊሽ ሌክሲከን
-