የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 1 ገጽ 14
  • የአምላክ ወዳጅ እንድንሆን የሚያስችል እውቀት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ ወዳጅ እንድንሆን የሚያስችል እውቀት
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፈጣሪያችን የግል ስም አለው
  • ይሖዋ አፍቃሪ አምላክ ነው
  • ይሖዋ ይቅር ባይ አምላክ ነው
  • ይሖዋ ጸሎታችንን መስማት ያስደስተዋል
  • ‘እርስ በርስ በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • የይሖዋ ይቅርታ ወደር የለውም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • አምላክ ማን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 1 ገጽ 14

የአምላክ ወዳጅ እንድንሆን የሚያስችል እውቀት

ፈጣሪያችን ማንነት የሌለው ኃይል አይደለም። ማራኪ የሆኑ ባሕርያት አሉት። ስለ እሱ እንድንማርና ወደ እሱ እንድንቀርብ ይፈልጋል። (ዮሐንስ 17:3፤ ያዕቆብ 4:8) ስለ ማንነቱ ብዙ ነገር ያሳወቀን ለዚህ ነው።

ፈጣሪያችን የግል ስም አለው

“ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣ አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ ሰዎች ይወቁ።”—መዝሙር 83:18

መጽሐፍ ቅዱስ፣ እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ብቻ እንደሆነ ያስተምራል። ጽንፈ ዓለምንም ሆነ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ የፈጠረው እሱ ነው። መመለክ ያለበት እሱ ብቻ ነው።—ራእይ 4:11

ይሖዋ አፍቃሪ አምላክ ነው

ይሖዋ የተባለው የፈጣሪ ስም በሂንዲ፣ በፑንጃብኛ፣ በጉጅራቲ፣ በቴሉጉ፣ በታሚል እና በአማርኛ ቋንቋዎች ሲጻፍ።

“አምላክ ፍቅር ነው።”—1 ዮሐንስ 4:8

ይሖዋ በመጽሐፍ ቅዱስና በዙሪያችን ባሉ የፍጥረት ሥራዎቹ አማካኝነት ባሕርያቱን ገልጾልናል። ዋነኛ ባሕርይው ፍቅር ነው። ፍቅር የማንነቱ መገለጫ ነው። ስለ ይሖዋ ይበልጥ ባወቅን መጠን ይበልጥ እየወደድነው እንሄዳለን።

ይሖዋ ይቅር ባይ አምላክ ነው

“አንተ . . . ይቅር ለማለት ዝግጁ [ነህ]።”—ነህምያ 9:17

ይሖዋ ፍጹም እንዳልሆንን ያውቃል። ስለዚህ እኛን “ይቅር ለማለት ዝግጁ” ነው። በጥፋታችን እንደተጸጸትን ከነገርነውና መጥፎ ነገር ማድረጋችንን ለማቆም የምንችለውን ሁሉ ካደረግን ይቅር ይለናል፤ የቀድሞ ኃጢአታችንን እንደገና አያነሳብንም።—መዝሙር 103:12, 13

ይሖዋ ጸሎታችንን መስማት ያስደስተዋል

“ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣ . . . ቅርብ ነው። . . . እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል።”—መዝሙር 145:18, 19

ይሖዋ ለየት ያሉ የአምልኮ ሥርዓቶች በመፈጸም ወይም የተለያዩ ሃይማኖታዊ ምስሎች ተጠቅመን እንድናመልከው አይጠብቅብንም። አፍቃሪ የሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው ሲናገሩ እንደሚያዳምጧቸው ሁሉ እሱም ስንጸልይ ያዳምጠናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ