-
ከባድ ኃጢአት ብትፈጽም ምን ማድረግ ይኖርብሃል?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ይሖዋ ለኃጢአተኞች ምሕረት ያደርጋል
ከባድ ኃጢአት የፈጸመ ሰው ከይሖዋ መሥፈርቶች ጋር ተስማምቶ ለመኖር ፈቃደኛ ካልሆነ ከጉባኤው ይወገዳል። እንዲህ ካለው ሰው ጋር ጊዜ አናሳልፍም። አንደኛ ቆሮንቶስ 5:6, 11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው ሁሉ ንስሐ ከማይገባ ኃጢአተኛ ጋር ጊዜ ማሳለፍም በጉባኤ ውስጥ ባሉት ላይ ምን ጉዳት ይኖረዋል?
ይሖዋ ፍጹም ላልሆኑ ኃጢአተኞች ምሕረት ያሳያል፤ ሽማግሌዎችም ከጉባኤ የተወገዱትን ለመርዳት ጥረት በማድረግ የእሱን ምሳሌ ይከተላሉ። ብዙዎች የተሰጣቸው ተግሣጽ ቢያሳዝናቸውም ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ስለረዳቸው ወደ ጉባኤው ተመልሰዋል።—መዝሙር 141:5
• ይሖዋ ኃጢአት የፈጸሙ ሰዎችን የሚይዝበት መንገድ ፍትሐዊ፣ መሐሪና አፍቃሪ መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው?
5. ንስሐ ከገባን ይሖዋ ይቅር ይለናል
ኢየሱስ፣ ይሖዋ ንስሐ ለገባ ኃጢአተኛ ያለውን አመለካከት የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል። ሉቃስ 15:1-7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይህ ጥቅስ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምርሃል?
ሕዝቅኤል 33:11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
-
-
ምንጊዜም ለይሖዋ ታማኝ ሁንለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
1. ሌሎች ሰዎች ለይሖዋ ያለንን ታማኝነት ሊፈትኑት የሚችሉት እንዴት ነው?
አንዳንድ ሰዎች ይሖዋን ማገልገላችንን እንድናቆም ለማድረግ ይሞክራሉ። እንዲህ ለማድረግ የሚሞክሩት እነማን ናቸው? ከእውነት ቤት የወጡ አንዳንድ ሰዎች እምነታችንን ለማዳከም ሲሉ ስለ አምላክ ድርጅት ውሸት ይናገራሉ። እንዲህ ያሉት ሰዎች ከሃዲዎች ተብለው ይጠራሉ። በተጨማሪም አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች ስለ እኛ የሐሰት መረጃዎችን በማናፈስ አስተዋይ ያልሆኑ ሰዎች ከእውነት ቤት እንዲወጡ ለማድረግ ይሞክራሉ። እንዲህ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር መከራከር እንዲሁም ጽሑፋቸውን ማንበብ፣ ድረ ገጻቸውን መጎብኘት ወይም ቪዲዮዎቻቸውን መመልከት አደገኛ ነው። ኢየሱስ ሌሎች ይሖዋን በታማኝነት እንዳያገለግሉ እንቅፋት የሚፈጥሩ ሰዎችን አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፦ “ተዉአቸው፤ እነሱ ዕውር መሪዎች ናቸው። ስለዚህ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ።”—ማቴዎስ 15:14
2. የምናደርጋቸው ውሳኔዎች ለይሖዋ ያለንን ታማኝነት ሊያሳዩ የሚችሉት እንዴት ነው?
ለይሖዋ ያለን ፍቅር ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ እንዳይኖረን እንድንጠነቀቅ ያነሳሳናል። ሥራችን፣ የምንካፈልበት እንቅስቃሴ አሊያም አባል የሆንበት ድርጅት ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ምንም ንክኪ ሊኖረው አይገባም። ይሖዋ ‘ሕዝቤ ሆይ፣ ከታላቂቱ ባቢሎን ውጡ’ በማለት አስጠንቅቆናል።—ራእይ 18:2, 4
ጠለቅ ያለ ጥናት
ማንም ሰው ለይሖዋ ያለህን ታማኝነት እንዳያዳክመው መጠንቀቅ የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን። በተጨማሪም ከታላቂቱ ባቢሎን በመውጣት ታማኝነትህን ማሳየት የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።
3. ሐሰተኛ አስተማሪዎች እንዳያታልሉህ ተጠንቀቅ
ስለ ይሖዋ ድርጅት መጥፎ ነገር ብንሰማ ምን ማድረግ ይኖርብናል? ምሳሌ 14:15ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
የምንሰማውን ነገር ሁሉ ማመን የሌለብን ለምንድን ነው?
ሁለተኛ ዮሐንስ 9-11ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ከሃዲዎችን በተመለከተ ምን አቋም ሊኖረን ይገባል?
ከከሃዲዎች ጋር በአካል ባንገናኝ እንኳ እነሱ ለሚያስተምሩት ትምህርት ልንጋለጥ የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
ይሖዋ ስለ እሱ ወይም ስለ ድርጅቱ ለሚነገር መጥፎ ወሬ ጆሮ ብንሰጥ ምን የሚሰማው ይመስልሃል?
4. አንድ ወንድም ኃጢአት በሚሠራበት ጊዜ ለአምላክ ታማኝ እንደሆንክ አሳይ
-