-
ጋይዮስ ወንድሞቹን የረዳበት መንገድመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ግንቦት
-
-
እነዚህ እንግዶች ሚስዮናውያን፣ የዮሐንስ መልእክተኞች አሊያም ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች ሊሆኑ ይችላሉ። ሁኔታው ምንም ይሁን ምን፣ እነዚህ ሰዎች ጉዞውን ያደረጉት ለምሥራቹ ሲሉ ነበር። ዮሐንስ ስለ እነሱ ሲናገር “የወጡት ለስሙ ሲሉ ነው” ብሏል። (3 ዮሐ. 7) ዮሐንስ ቀደም ሲል ስለ አምላክ ስለጠቀሰ (ቁጥር 6ን ተመልከት) “ለስሙ ሲሉ” የሚለው አገላለጽ የይሖዋን ስም የሚያመለክት ይመስላል። በመሆኑም እነዚህ ወንድሞች የክርስቲያን ጉባኤ አባል ከመሆናቸው አንጻር ጥሩ አቀባበል ሊደረግላቸው ይገባል። ዮሐንስ እንደተናገረው “በእውነት ውስጥ አብረን የምንሠራ እንሆን ዘንድ እንዲህ ላሉ ሰዎች የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ የማሳየት ግዴታ አለብን።”—3 ዮሐ. 8
-
-
ጋይዮስ ወንድሞቹን የረዳበት መንገድመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ግንቦት
-
-
አንደኛ፣ አብዛኞቻችን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያወቅነው ይህንን እውነት ለማስተማር ሲሉ ወደተለያዩ ቦታዎች ይጓዙ በነበሩ ታማኝ ክርስቲያኖች አማካኝነት ነው። እርግጥ ነው፣ በዛሬው ጊዜ ለምሥራቹ ሲሉ ረጅም ርቀት የሚጓዙት ሁሉም ክርስቲያኖች አይደሉም። ይሁን እንጂ እንዲህ ያለ ጉዞ የሚያደርጉትን፣ በሆነ መንገድ በመደገፍ ወይም በማበረታታት የጋይዮስን አርዓያ መከተል እንችላለን። ለምሳሌ የወረዳ የበላይ ተመልካቹንና ሚስቱን ወይም ደግሞ በአገራቸው ውስጥ አሊያም ከአገራቸው ውጭ የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉባቸው ቦታዎች ተዛውረው ለሚያገለግሉ ወንድሞችና እህቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንችል ይሆናል። እንግዲያው ሁላችንም “የእንግዳ ተቀባይነትን ባሕል [እናዳብር]።”—ሮም 12:13፤ 1 ጢሞ. 5:9, 10
-