የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጋይዮስ ወንድሞቹን የረዳበት መንገድ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ግንቦት
    • ጋይዮስ የጉባኤ የበላይ ተመልካች ሊሆን ይችላል፤ በእርግጥ በደብዳቤው ላይ ይህን በቀጥታ የሚናገር ሐሳብ አናገኝም። ጋይዮስ የማያውቃቸውን ወንድሞች እንኳ ተቀብሎ በማስተናገዱ ዮሐንስ አመስግኖታል። ጋይዮስ ይህን ማድረጉ ታማኝነቱን የሚያረጋግጥ እንደሆነ ዮሐንስ ተሰምቶታል፤ ምክንያቱም እንግዳ ተቀባይነት ከጥንት ጀምሮ የአምላክ አገልጋዮች ተለይተው የሚታወቁበት ምልክት ነው።—ዘፍ. 18:1-8፤ 1 ጢሞ. 3:2፤ 3 ዮሐ. 5

      ጋይዮስ፣ ወንድሞችን በእንግድነት በመቀበሉ ዮሐንስ ያደነቀው መሆኑ የሚጠቁመው ነገር አለ፤ ይኸውም ክርስቲያኖች ሐዋርያው ዮሐንስ ካለበት ቦታ ወደተለያዩ ጉባኤዎች አዘውትረው እንደሚመላለሱና ስላጋጠማቸው ነገር ለዮሐንስ ይነግሩት እንደነበረ ያሳያል። ዮሐንስ ስለ ጉባኤዎቹ ይሰማ የነበረው በዚህ መንገድ ሳይሆን አይቀርም።

      ከቦታ ቦታ የሚጓዙ ክርስቲያኖች የእምነት አጋሮቻቸው ዘንድ ማረፍ ይመርጡ እንደነበር ግልጽ ነው። ምክንያቱም በወቅቱ የነበሩት የእንግዳ ማረፊያዎች መጥፎ ስም ያተረፉ ከመሆኑም ሌላ መስተንግዷቸውም ጥሩ አልነበረም፤ በዚያ ላይ ደግሞ የሥነ ምግባር ብልግና የሚፈጸምባቸው ቦታዎች ነበሩ። በመሆኑም ጥበበኛ የሆኑ ተጓዦች በተቻለ መጠን ወዳጆቻቸው ጋ ለማረፍ ይፈልጉ ነበር፤ ከቦታ ቦታ የሚጓዙ ክርስቲያኖችም የእምነት አጋሮቻቸው ዘንድ ያርፉ ነበር።

  • ጋይዮስ ወንድሞቹን የረዳበት መንገድ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ግንቦት
    • ሦስተኛ፣ የሚያጋጥማቸውን ተቃውሞ ተቋቁመው ይሖዋን በታማኝነት የሚያገለግሉ የእምነት አጋሮቻችን ሊመሰገኑና ልባዊ አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል። ሐዋርያው ዮሐንስ ጋይዮስን እንዳበረታታውና እያደረገ ያለው ነገር ትክክል መሆኑን እንዳረጋገጠለት ጥያቄ የለውም። በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ ያሉ ሽማግሌዎች፣ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ‘እንዳይዝሉ’ በማበረታታት የዮሐንስን ምሳሌ መከተል ይኖርባቸዋል።—ኢሳ. 40:31፤ 1 ተሰ. 5:11

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ