-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2003 | ታኅሣሥ 15
-
-
ክፉዎቹ መላእክት ከሰማይ ከመባረራቸውም በፊት ከአምላክ ቤተሰብ ተገልለውና እገዳ ተጥሎባቸው እንደነበረ ልብ ሊባል ይገባዋል። ለምሳሌ ያህል ይሁዳ 6 እነዚህ ክፉ መላእክት በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንኳን “በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ” እየተጠበቁ እንደነበረ ይናገራል። በተመሳሳይም 2 ጴጥሮስ 2:4 “እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጕድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ” እንደሰጣቸው ይናገራል።b
-
-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ—2003 | ታኅሣሥ 15
-
-
b ሐዋርያው ጴጥሮስ ይህን ሲል በመንፈሳዊ መገለልን “በወኅኒ” ከመታሰር ጋር ማወዳደሩ ነበር እንጂ ወደፊት አጋንንት ለአንድ ሺህ ዓመታት ስለሚታሰሩበት ስለ ‘ጥልቁ’ እየተናገረ አልነበረም።—1 ጴጥሮስ 3:19, 20፤ ሉቃስ 8:30, 31፤ ራእይ 20:1-3
-