የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የእሳት ሐይቅ ምንድን ነው? ገሃነም ነው? ወይስ ሲኦል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
      • ዲያብሎስ፦ (ራእይ 20:10) ዲያብሎስ መንፈሳዊ አካል ያለው ፍጥረት እንደመሆኑ መጠን እሳት ሊጎዳው አይችልም።—ዘፀአት 3:2፤ መሳፍንት 13:20

  • የእሳት ሐይቅ ምንድን ነው? ገሃነም ነው? ወይስ ሲኦል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    • “ከዘላለም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሠቃያሉ” ሲባል ምን ማለት ነው?

      የእሳት ሐይቅ ዘላለማዊ ጥፋትን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አባባል ከሆነ ዲያብሎስ፣ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ በእሳት ሐይቅ ውስጥ “ከዘላለም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት [እንደሚሠቃዩ]” መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ለምንድን ነው? (ራእይ 20:10) በዚህ ጥቅስ ላይ የተገለጸው ሥቃይ፣ ቃል በቃል እንዳልሆነ የሚጠቁሙ አራት ምክንያቶችን እስቲ እንመልከት፦

      1. ሰይጣን ለዘላለም እንዲሠቃይ ከተፈለገ ለዘላለም እንዲኖር ይደረጋል ማለት ነው። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ሰይጣን እንዳልነበረ እንደሚደረግ ይኸውም ከሕልውና ውጭ እንደሚሆን ነው።—ዕብራውያን 2:14

      2. ለዘላለም መኖር ቅጣት ሳይሆን የአምላክ ስጦታ ነው።—ሮም 6:23

      3. አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ምሳሌያዊ ነገሮች በመሆናቸው ቃል በቃል ሥቃይ ሊሰማቸው አይችልም።

      4. በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከሚገኙት ሌሎች ሐሳቦች እንደምንረዳው ዲያብሎስ እንደሚሠቃይ የሚገልጸው ሐሳብ ለዘላለም እንደሚታገድ ወይም እንደሚጠፋ የሚያመለክት ነው።

      በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘መሠቃየትን’ ለማመልከት የተሠራበት ቃል “መታገድን” ጭምር ሊያመለክት ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ በማቴዎስ 18:34 ላይ የተጠቀሱትን ‘የወኅኒ ቤት ጠባቂዎች’ ለማመልከት የገባው ቃል በግሪክኛ ‘የሚያሠቃዩ ሰዎች’ (የ1954 ትርጉም) የሚል ትርጉም አለው፤ ይህም በግሪክኛ ‘መሠቃየት’ እና ‘መታገድ’ በሚሉት ቃላት መካከል ዝምድና እንዳለ ይጠቁማል። ከዚህም በተጨማሪ፣ በማቴዎስ 8:29 ላይ የተጠቀሰው ‘መሠቃየት’ ተመሳሳይ ዘገባ በያዘው በሉቃስ 8:30, 31 ላይ “ጥልቁ” ተብሏል፤ “ጥልቁ” የሚለው ቃል ደግሞ እንቅስቃሴ ማድረግ አለመቻልን ወይም መሞትን የሚያመለክት ምሳሌያዊ ቦታ ነው። (ሮም 10:7፤ ራእይ 20:1, 3) እንዲያውም በራእይ መጽሐፍ ውስጥ በበርካታ ቦታዎች ላይ ‘ሥቃይ’ የሚለው ቃል የተሠራበት ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ነው።—ራእይ 9:5፤ 11:10፤ 18:7, 10

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ