የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ በሙሉ ነፍስ የምታቀርቡትን አገልግሎት ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥቅምት 15
    • 5. የሐዋርያቱ ምሳሌ ሁሉም ሰው በአገልግሎት እኩል መጠን ያለው ነገር እንደማያከናውን የሚያሳየው እንዴት ነው?

      5 በሙሉ ነፍስ ማገልገል ማለት ሁላችንም በአገልግሎት የምናከናውነው መጠን እኩል መሆን አለበት ማለት ነውን? የእያንዳንዱ ሰው ሁኔታና ችሎታ ስለሚለያይ በፍጹም እንደዚያ ማለት አይደለም። የታመኑትን የኢየሱስ ሐዋርያት ምሳሌ ተመልከት። ሁሉም እኩል መጠን ያለው አገልግሎት ማከናወን አልቻሉም ነበር። ለምሳሌ ያህል ስለ ቀነናዊው ስምዖንና ስለ እልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ እምብዛም የምናውቀው ነገር የለም። ምናልባትም በሐዋርያነት ያደረጉት እንቅስቃሴ ውስን ይሆናል። (ማቴዎስ 10:​2-4) በአንጻሩ ደግሞ ጴጥሮስ ብዙ ከባድ ኃላፊነቶችን መቀበል ችሎ ነበር፤ ኢየሱስም ‘የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻ’ ሰጥቶታል። (ማቴዎስ 16:​19) ይሁንና ጴጥሮስ ከሌሎች ልቆ ይታይ ነበር ማለት አይደለም። ዮሐንስ ስለ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በተገለጠለት ራእይ ውስጥ (በ96 እዘአ) ‘የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም የተጻፈባቸው’ አሥራ ሁለት የመሠረት ድንጋዮች ተመልክቷል።a (ራእይ 21:​14) አንዳንዶቹ የበለጠ መሥራት ችለው የነበረ ቢሆንም ሁሉም ሐዋርያት ያከናወኑት አገልግሎት በይሖዋ ፊት ትልቅ ዋጋ ነበረው።

  • ይሖዋ በሙሉ ነፍስ የምታቀርቡትን አገልግሎት ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥቅምት 15
    • a በይሁዳ ፋንታ የተተካው ሐዋርያ ማትያስ ስለሆነ በአሥራ ሁለቱ የመሠረት ድንጋይ ላይ ከሰፈሩት ስሞች መካከል አንዱ የእርሱ እንጂ የጳውሎስ አይሆንም። ጳውሎስ ሐዋርያ ቢሆንም ከአሥራ ሁለቱ አንዱ አልነበረም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ