የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አንጸባራቂዋ ከተማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 6. (ሀ) ዮሐንስ የከተማይቱን መለካት እንዴት በማለት ገልጾአል? ይህስ መለካት ምን ያመለክታል? (ለ) መለኪያው ‘የሰው ልክና የመላእክት ልክ’ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? (የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።)

      6 ዮሐንስ ትረካውን በመቀጠል እንዲህ ይላል:- “የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው። ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፣ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት አሥራ ሁለትም ሺህ ምዕራፍ ሆነች ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው። ቅጥርዋንም ለካ፣ መቶ አርባ አራት ክንድ በሰው ልክ፣ እርሱም በመልአክ ልክ።” (ራእይ 21:15-17) የቤተ መቅደሱ መለካት ይሖዋ ለቤተ መቅደሱ ያወጣው ዓላማ ስለመፈጸሙ ዋስትና እንደሚሆን ተገልጾአል። (ራእይ 11:1) አሁን ደግሞ መልአኩ አዲሲቱን ኢየሩሳሌም መለካቱ ይሖዋ ለዚህች ታላቅ ከተማ ያወጣው ዓላማ የማይለወጥ መሆኑን ያመለክታል።a

      7. የከተማይቱ ልክ አስደናቂ የሆነው ለምንድን ነው?

      7 ይህች ከተማ በጣም አስደናቂ የሆነች ከተማ ነች። ቁመትዋ፣ ስፋትዋና ከፍታዋ እኩል ሲሆን ዙሪያዋ 12,000 ምዕራፍ ወይም 2,200 ኪሎ ሜትር ነው። ዙሪያዋን 144 ክንድ ወይም 210 ጫማ ከፍታ ባለው ቅጥር ታጥራለች። እንዲህ ያለ መጠን ያለው እውነተኛ ከተማ ሊኖር አይችልም። ዘመናዊቱን ኢየሩሳሌም 14 ጊዜ የሚያጥፍ ስፋት ያለውና 560 ኪሎ ሜትር ያህል ከፍታ ያለው ሰማይ ጠቀስ ከተማ ይሆናል። የራእይ መጽሐፍ የተገለጸው በምልክቶች ነው። ታዲያ እነዚህ ልኮች ስለ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ምን ያመለክታሉ?

      8. (ሀ) የከተማይቱ ቅጥር 144 ክንድ ከፍታ ያለው መሆኑ (ለ) የከተማይቱ ልክ 12,000 ምዕራፍ መሆኑ (ሐ) የከተማይቱ ቅርጽ በሁሉም በኩል የተስተካከለ ኩብ መሆኑ ምን ያመለክታል?

      8 144 ክንድ ከፍታ ያለው ቅጥር ከተማይቱ የተገነባችው በ144,000ዎቹ የአምላክ መንፈሣዊ ልጆች አባልነት እንደሆነ ያሳስበናል። የዚህ ከተማ ቁመት፣ ስፋትና ከፍታ 12,000 ምዕራፍ ነው። አስራ ሁለት ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ውስጥ የድርጅታዊ ዝግጅት ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል። ስለዚህ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የአምላክን ዘላለማዊ ዓላማ ለማስፈጸም በከፍተኛ ደረጃ የተዋቀረች ድርጅታዊ ዝግጅት ነች። አዲሲቱ ኢየሩሳሌምና ኢየሱስ ክርስቶስ የይሖዋን መንግሥታዊ ድርጅት ይመሠርታሉ። በተጨማሪም የከተማይቱ ቅርጽ ማለትም ርዝመት፣ ስፋትና ከፍታ እኩል ነው። በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ውስጥ የይሖዋ መገኘት ምሳሌ የሆኑት ነገሮች የሚገኙበት ቅድስተ ቅዱሳን ርዝመቱ፣ ስፋቱና ከፍታው እኩል ነበር። (1 ነገሥት 6:19, 20) የይሖዋ ክብር ያበራባት አዲሲቱ ኢየሩሳሌምም ርዝመቱ፣ ስፋቱና ከፍታው እኩል የሆነ የኩብ ቅርጽ ያላት መሆንዋ በጣም ተገቢ ነው። ልኮችዋ ሁሉ የተመጣጠኑ ናቸው። ምንም ዓይነት ጉድለት ወይም ወጣ ገባ የሆነ ነገር የሌለባት ከተማ ነች።—ራእይ 21:22

  • አንጸባራቂዋ ከተማ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • a እዚህ ላይ ያገለገለው መለኪያ “የሰው ልክ” እና “የመልአክ ልክ” መሆኑ ከተማይቱ በአባልነት የተገነባችው መጀመሪያ ሰዎች በነበሩትና በኋላ እንደ መላእክት መንፈሳዊ ፍጥረቶች በሚሆኑት 144,000ዎች ከመሆኑ ጋር ዝምድና ያለው ሊሆን ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ