-
አንጸባራቂዋ ከተማራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
9. ዮሐንስ ከተማይቱ የታነጸችባቸውን የግንባታ ዕቃዎች ምን በማለት ገልጾአል?
9 ዮሐንስ መግለጫውን በመቀጠል እንዲህ ይላል:- “ቅጥርዋም ከኢያስጲድ የተሠራ ነበረ፣ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች። የከተማይቱም ቅጥር መሠረት በከበረ ድንጋይ ሁሉ ተጌጦ ነበር፣ ፊተኛው መሠረት ኢያስጲድ፣ ሁለተኛው ሰንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ፣ አምስተኛው ሰርዶንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ወራውሬ፣ አሥረኛው ክርስጵራስስ፣ አሥራ አንደኛው ያክንት፣ አሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ። አሥራ ሁለቱም ደጆች አሥራ ሁለት ዕንቆች ነበሩ፣ እያንዳንዱ ደጅ ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም አደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረ።”—ራእይ 21:18-21
10. ከተማይቱ የተሰራችው በኢያስጲድ፣ በወርቅና በተለያዩ ‘የከበሩ ድንጋዮች’ መሆኑ ምን ያመለክታል?
10 የከተማይቱ አሠራር በእውነትም በጣም አንጸባራቂ ነው። ርካሽና ተራ ስለሆኑ እንደ ሸክላና እንደ ድንጋይ ስላሉት ምድራዊ የሕንጻ መሣሪያዎች ሳይሆን ስለ ኢያስጲድ፣ ስለተጣራ ወርቅና ስለተለያዩ ‘የከበሩ ድንጋዮች’ እናነባለን። እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች ሁሉ ሰማያዊ የሕንጻ መሣሪያዎችን የሚያመለክቱ መሆናቸው ተገቢ ነው። ከዚህ ይበልጥ አስደናቂ የሆነና የተዋበ ነገር ሊኖር አይችልም። የጥንቱ የቃል ኪዳን ታቦት በወርቅ የተለበጠ ነበር። በተጨማሪም ወርቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም ውድና ጥሩ የሆኑ ነገሮችን ያመለክታል። (ዘጸአት 25:11፤ ምሳሌ 25:11፤ ኢሳይያስ 60:6, 17) መላዋ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፣ አደባባዮችዋ እንኳን ሳይቀሩ እንደ መስተዋት ከጠራ ወርቅ የተሠሩ ናቸው። ለግምት እንኳን የሚያስቸግር ከፍተኛ ዋጋና ውበት እንዳላት ያመለክታል።
-
-
አንጸባራቂዋ ከተማራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
12. (ሀ) የከተማይቱ መሠረቶች በ12 የከበሩ ድንጋዮች ያጌጡ መሆናቸው (ለ) የከተማይቱ በሮች ዕንቁ መሆናቸው ምን ያመለክታል?
12 የከተማዋ መሠረቶች እንኳን በ12 የከበሩ ድንጋዮች ያጌጡ ስለሆኑ በጣም የተዋቡ ናቸው። ይህም በበዓል ቀናት እዚህ ላይ ከተገለጹት ጋር በሚመሳሰሉ አሥራ ሁለት የተለያዩ እንቁዎች ያጌጠ ኤፉድ ይለብስ የነበረውን የአይሁድ ሊቀ ካህናት ያስታውሰናል። (ዘጸአት 28:15-21) ይህ በአጋጣሚ ብቻ የሆነ መመሳሰል አይደለም። ታላቁ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ “መብራት” የሆነላት አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የምታከናውነውን ክህነታዊ አገልግሎት ጎላ አድርጎ የሚያሳይ ነው። (ራእይ 20:6፤ 21:23፤ ዕብራውያን 8:1) በተጨማሪም የኢየሱስ የሊቀ ካህንነት አገልግሎት ጥቅሞች ለሰው ልጆች የሚተላለፉት በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም በኩል ነው። (ራእይ 22:1, 2) እያንዳንዳቸው ከፍተኛ ውበት ካላቸው ዕንቁዎች የተሠሩት የከተማይቱ 12 በሮችም ኢየሱስ መንግሥቱን ከፍተኛ ዋጋ ባለው ዕንቁ በመመሰል የተናገረውን ምሳሌ ያስታውሰናል። በእነዚህ በሮች የሚገባ ሁሉ ለመንፈሣዊ ነገሮች ከፍተኛ ዋጋና ትልቅ አድናቆት ያሳየ ሰው ነው።—ማቴዎስ 13:45, 46፤ ከኢዮብ 28:12, 17, 18 ጋር አወዳድር።
-