የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የራእይን መጽሐፍ በማንበብ ተደሰቱ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ታኅሣሥ 1
    • 16. የዮሐንስ ራእይ የመደምደሚያ ምዕራፎች የተለየ የደስታ ምክንያት የሚሆኑን ለምንድን ነው?

      16 የራእይን መጽሐፍ በደስታ የሚያነብቡ ሰዎች የሚፈነድቁት ስለ ክብራማው የአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ተስፋችን የሚናገሩትን የመደምደሚያ ምዕራፎች ሲያነብቡ ብቻ ነው። ይህ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ጽድቅ የሰፈነበት ንጉሣዊ የሰማይ መስተዳደርና በዚያ ሥር የሚተዳደር አዲስ ንጹሕ ሰብዓዊ ኅብረተሰብ ማለት ነው። ይህም ‘ሁሉን ለሚገዛው አምላክ’ ለይሖዋ ክብር የሚያመጣ ነው። (ራእይ 21:​22) እነዚህ ድንቅ ተከታታይ ራእይዎች ሲደመደሙ መልእክተኛው መልአክ ለዮሐንስ እንደሚከተለው ብሎታል:- “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፣ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ። እነሆም፣ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”​—⁠ራእይ 22:​6, 7

  • የራእይን መጽሐፍ በማንበብ ተደሰቱ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ታኅሣሥ 1
    • 18, 19. (ሀ) ኢየሱስ ገና መምጣት የሚኖርበት ለምንድን ነው? ዮሐንስ የተናገረው የየትኛው ተስፋ ተካፋዮች እንሆናለን? (ለ) ይሖዋስ ገና ወደፊት ‘የሚመጣው’ ለምን ዓላማ ነው?

      18 ኢየሱስ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ “ቶሎ ብዬ እመጣለሁ” እያለ ደጋግሞ ተናግሯል። (ራእይ 2:​16፤ 3:​11፤ 22:​7, 20ሀ) በታላቂቱ ባቢሎን፣ በሰይጣን የፖለቲካ ሥርዓትና ዛሬ በመሲሐዊ መንግሥቱ አማካኝነት ለተገለጠው የይሖዋ ሉዓላዊነት ለመገዛት አሻፈረኝ በሚሉ ሰዎች ሁሉ ላይ ፍርዱን ለማስፈጸም ገና ይመጣል። እኛም ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ድምፃችንን በማስተባበር “አሜን፣ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና” እንላለን።​—⁠ራእይ 22:​20ለ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ