-
ራእይ እና አንተራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
3, 4. መልአኩ በመቀጠል ለዮሐንስ ምን ነገረው? ቅቡዓን ቀሪዎች ይህን ቃል የታዘዙት እንዴት ነው?
3 ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይቀጥላል:- “ለእኔም:- ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው። ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፣ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ፣ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፣ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ አለ።”—ራእይ 22:10, 11
-
-
ራእይ እና አንተራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
5. (ሀ) ሰዎች በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተገለጸውን ምክርና ማስጠንቀቂያ አንሰማም ቢሉስ? (ለ) ቅኖችና ጻድቃን የሆኑ ሰዎች ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?
5 ሰዎች በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተገለጹትን ማስጠንቀቂያዎችና ምክሮች ችላ ለማለት ከመረጡ በምርጫቸው ይግፉበት። “ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ።” በዚህ ስድ ዓለም እድፍ እንደተጨማለቁ ለመኖር ከመረጡ እንደተጨማለቁ ሊሞቱ ይችላሉ። በቅርብ ጊዜ ውስጥ የይሖዋ ፍርድ በታላቂቱ ባቢሎን ጥፋት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል። ቅን ልብ ያላቸው ሁሉ “እግዚአብሔርን [“ይሖዋን፣” NW] ፈልጉ፣ ጽድቅንም ፈልጉ፣ ትሕትናንም ፈልጉ። ምናልባት በእግዚአብሔር [“በይሖዋ፣” NW] ቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል” የሚለውን የነቢዩን ምክር ለመፈጸም ይትጉ። (ሶፎንያስ 2:3) ሕይወታቸውን ለይሖዋ የወሰኑ ሁሉ ደግሞ “ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፣ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ” የሚለውን ምክር በትጋት ይፈጽሙ። ጠቢባን የሆኑ ሁሉ ከኃጢአት የሚገኝ ማንኛውም ጊዜያዊ ጥቅም የጽድቅንና የቅድስናን መንገድ የሚከታተሉ ሰዎች ከሚያገኙአቸው ዘላቂ በረከቶች ጋር ሊወዳደሩ እንደማይችሉ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፣ ራሳችሁን ፈትኑ” ይላል። (2 ቆሮንቶስ 13:5) በመረጣችሁትና ስትመላለሱበት በቆያችሁበት መንገድ ላይ የተመሠረተውን ሽልማት ትቀበላላችሁ።—መዝሙር 19:9-11፤ 58:10, 11
-