የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የኢየሱስን ስም አጥብቆ መያዝ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 14. (ሀ) የክርስቲያን ጉባኤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ ከእነማን ጋር መታገል አስፈልጎት ነበር? እነዚህንስ ሐዋርያው ጳውሎስ የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) የተገነጠሉ ቡድኖችን ለመከተል ያዘነበሉ ሁሉ የትኛውን የኢየሱስ ቃል መከተል ይኖርባቸዋል?

      14 የክርስቲያን ጉባኤ ገና ከመጀመሪያው አንስቶ በለስላሳና በሚሸነግል አንደበታቸው ክርስቲያኖች ይሖዋ ባዘጋጀው የመገናኛ መስመር አማካኝነት የተማሩትን “ትምህርት የሚቃወሙ መለያየትንና ማሰናከያን” የሚያመጡትን ትዕቢተኛ ከሃዲዎች ለመቋቋም ተገድዶ ነበር። (ሮሜ 16:17, 18) ሐዋርያው ጳውሎስ በመልእክቶቹ ሁሉ ስለዚህ አደጋ ሳያስጠነቅቅ አላለፈም።a ኢየሱስ እውነተኛውን ጉባኤ ወደ ክርስቲያናዊ ንጽሕናና አንድነት በመለሰበት በዚህ ዘመንም ቢሆን የመናፍቅነት አሳሳቢነት ፈጽሞ አልተወገደም። ስለዚህ የተገነጠሉ ቡድኖችን ለመከተልና ኑፋቂያዊ ድርጅት ለማቋቋም አስበው የነበሩ ካሉ የሚከተለውን የኢየሱስ ቃል መፈጸም ይኖርባቸዋል:- “እንግዲህ ንሥሐ ግባ፣ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፣ በአፌም ሠይፍ እዋጋቸዋለሁ።”—ራእይ 2:16

  • የኢየሱስን ስም አጥብቆ መያዝ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 16. (ሀ) በከሃዲዎች ተጽእኖ ምክንያት የሚወላውሉ ሰዎች ፈጥነው ንስሐ መግባት የሚኖርባቸው ለምንድን ነው? (ለ) ንስሐ ለመግባት እምቢተኞች የሆኑ ሁሉ ምን ይደርስባቸዋል?

      16 በክህደት ትምህርት ምክንያት ወዲያና ወዲህ የሚዋልሉ ሁሉ ኢየሱስ ንስሐ እንዲገቡ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ፈጥነው ቢቀበሉ ጥሩ ነው። የክህደት ፕሮፓጋንዳ ክፉ መርዝ ስለሆነ ሊወገድ ይገባዋል። የክህደት ፕሮፓጋንዳ ኢየሱስ ለጉባኤው ከሚመግበው ንጹሕ፣ ጻድቅና ፍቅር የሞላበት እውነት የተለየ ነው። መሠረቱም ቅንዓትና ጥላቻ ነው። (ሉቃስ 12:42፤ ፊልጵስዩስ 1:15, 16፤ 4:8, 9) ንስሐ ለመግባት አሻፈረን የሚሉትን ግን ጌታ ኢየሱስ ‘ከአፉ በሚወጣው ረዥም ሠይፍ ይዋጋቸዋል።’ ኢየሱስ በምድር ላይ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ባሳለፈው የመጨረሻ ምሽት የጸለየለትን አንድነት ለማስጠበቅ ሕዝቦቹን በማበጠር ላይ ነው። (ዮሐንስ 17:20-23, 26) ከሃዲዎች በኢየሱስ ቀኝ እጅ ያሉት ኮከቦች የሚሰጡትን በፍቅር ላይ የተመሠረተ ምክር ስለማይቀበሉ ኢየሱስ “በውጭ ወዳለው ጨለማ” አውጥቶ በመጣል ከባድ የቅጣት ፍርድ ይፈጽምባቸዋል። በአምላክ ሕዝቦች መካከል እንደ እርሾ ሆነው እንዳይበክሉ ይወገዳሉ።—ማቴዎስ 24:48-51፤ 25:30፤ 1 ቆሮንቶስ 5:6, 9, 13፤ ራእይ 1:16

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ