የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ራእይ እና አንተ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 6. ይሖዋ ለራእይ መጽሐፍ አንባቢዎች ለመጨረሻ ጊዜ ምን አላቸው?

      6 አሁን የዘላለሙ ንጉሥ ይሖዋ በዚህ ትንቢት ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ ለራእይ መጽሐፍ አንባቢዎች በቀጥታ ተናገረ:- “እነሆ፣ በቶሎ እመጣለሁ፣ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን [“ደስተኞች፣” NW] ናቸው። ውሻዎችና አስማተኛዎች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።”—ራእይ 22:12-15

  • ራእይ እና አንተ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 8. (ሀ) ወደ “ሕይወት ዛፍ” የሚሄዱት እነማን ብቻ ናቸው? ይህስ ምን ማለት ነው? (ለ) እጅግ ብዙ ሰዎች ልብሳቸውን ያጠቡት እንዴት ነው? ንጹሕ አቋም የሚያገኙትስ እንዴት ነው?

      8 “ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ” መብት የሚኖራቸው በይሖዋ ዓይን ንጹሕ ሆነው ለመታየት ‘ልብሳቸውን ያጠቡት’ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው። በሰማያዊ ቦታቸው ሞት የማይደፍረው ሕይወት የማግኘት መብትና ሥልጣን ይሰጣቸዋል ማለት ነው። (ከዘፍጥረት 3:22-24፤ ከ⁠ራእይ 2:7⁠ና ከራእይ 3:4, 5 ጋር አወዳድር።) ሰብዓዊ ሞት ከሞቱ በኋላ ከሙታን ተነስተው ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ይገባሉ። 12ቱ መላእክት ሰማያዊ ተስፋ አለን እያሉ በሐሰትና በእርኩሰት የሚመላለሱትን ወደ ውጭ አስቀርተው እነዚህን ግን ወደ ውስጥ ያስገባሉ። በተጨማሪም በምድር ላይ ያሉት እጅግ ብዙ ሰዎች “ልብሳቸውን አጥበው በበጉ ደም” አንጽተዋል። ይህንን ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው መኖር ይገባቸዋል። ይህንንም የሚያደርጉት ይሖዋ እዚህ ላይ ማስጠንቀቂያ የሰጠባቸውን የእርኩሰት ሥራዎች በማስወገድና ኢየሱስ ለጉባኤዎች በላከው ሰባት መልእክቶች የሰጠውን ምክር በሥራ ላይ በማዋል ነው።—ራእይ 7:14፤ ምዕራፍ 2⁠ና 3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ