-
ራእይ እና አንተራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
15. ኢየሱስ ስለ እነዚህ ነገሮች “የምመሰክር እኔ ነኝ” ማለቱና ‘እነሆ ፈጥኜ እመጣለሁ’ ማለቱ ምን ትርጉም አለው?
15 አሁን ኢየሱስ አንድ የመጨረሻ ማበረታቻ መልእክት ይጨምራል:- “ይህን የሚመሰክር:- አዎን፣ በቶሎ እመጣለሁ ይላል።” (ራእይ 22:20ሀ) ኢየሱስ “የታመነውና እውነተኛው ምስክር” ነው። (ራእይ 3:14) በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ስለተገለጹት ራእዮች ከመሰከረ ራእዮቹ እውነት መሆን ይኖርባቸዋል። ኢየሱስም ሆነ ይሖዋ በቶሎ የሚመጡ መሆናቸውን በመደጋገም አጠንክረው ተናግረዋል። ኢየሱስ ለአምስተኛ ጊዜ መናገሩ ነው። (ራእይ 2:16፤ 3:11፤ 22:7, 12, 20) የሚመጡት በታላቂቱ ጋለሞታ፣ በፖለቲካዊ “ነገሥታትና” “የጌታችንንና [የይሖዋንና] የክርስቶስን መንግሥት” በሚቃወሙ ሁሉ ላይ የቅጣት ፍርድ ለመፈጸም ነው።—ራእይ 11:15፤ 16:14, 16፤ 17:1, 12-14
16. ይሖዋ አምላክና ኢየሱስ ፈጥነው እንደሚመጡ ስላወቅህ ምን ቆራጥ እርምጃ መውሰድ ይኖርብሃል?
16 ይሖዋ አምላክና ኢየሱስ በቶሎ እንደሚመጡ ማወቅህ ‘የይሖዋን ቀን ዘወትር እንድታስብ’ ሊያደርግህ ይገባል። (2 ጴጥሮስ 3:12) ይህ በሰይጣን ሥርዓት ሥር የሚተዳደረው ምድር ተደላድሎ የቆመ የሚመስለው ለጊዜው ብቻ ነው። በሰይጣን ሥር የሆኑትን የዓለማዊ ገዥዎች የሚያመለክተው ሰማይ ምንም ዓይነት የተሳካ ውጤት ያገኘ ቢመስልም በንኖ ይጠፋል። እነዚህ ሁሉ አላፊና ጠፊ የሆኑ ነገሮች ናቸው። (ራእይ 21:1) ዘላቂና ቋሚ የሆኑት ይሖዋ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የምትተዳደረው መንግሥቱና ቃል የገባልን አዲስ ዓለም ብቻ ናቸው። ለአንድ አፍታ እንኳን ይህን መዘንጋት አይገባህም!—1 ዮሐንስ 2:15-17
-
-
ራእይ እና አንተራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
19. አረጋዊው ሐዋርያው ዮሐንስ ምን የመደምደሚያ ቃል ተናግሮአል? እነዚህንስ ቃላት እንዴት መቀበል ይኖርብሃል?
19 ስለዚህ ከዮሐንስ ጋር ሆነን “አሜን፣ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ና” እያልን በጋለ ስሜት እንጸልያለን። አረጋዊው ሐዋርያ ዮሐንስ ደግሞ በመጨመር “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን” ይላል። (ራእይ 22:20ለ, 21) ይህን መጽሐፍ ለምታነቡ ሁሉ ይህንኑ እንመኛለን። ሁላችሁም ከልባችሁ “አሜን” ለማለት እንድትችሉ ታላቁ የራእይ መደምደሚያ ቅርብ ስለመሆኑ እምነት እንዲኖራችሁ እንመኛለን።
-