የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የሰይጣንን ጥልቅ ነገሮች” መጸየፍ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 8. (ሀ) ኢየሱስ በትያጥሮን ስለነበረችው “ኤልዛቤል” ምን ውሳኔ አስተላልፎ ነበር? (ለ) በዘመናችን ተገቢ ያልሆነ የሴቶች ተጽዕኖ የታየው እንዴት ነው?

      8 ኢየሱስ በመቀጠል በትያጥሮን ለነበሩት ሽማግሌዎች እንዲህ ይላቸዋል:- “ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም። እነሆ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፣ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ።” (ራእይ 2:21, 22) የመጀመሪያዋ ኤልዛቤል በአክዓብ ላይ እንደሰለጠነችና የአምላክ ፍርድ አስፈጻሚ የነበረውን ኢዩን እንደናቀች ሁሉ ይህም በትያጥሮን ጉባኤ የነበረው የሴቶች ተጽእኖ ባሎችንና ሽማግሌዎችን በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ሞክሮ ነበር። በትያጥሮን ጉባኤ የነበሩትም ሽማግሌዎች ይህን ትህትና የጎደለውን የኤልዛቤል ተጽእኖ በቸልታ የተመለከቱት ይመስላል። ኢየሱስ እዚህ ላይ ለእነርሱም ሆነ በዘመናችን ላለው ምድር አቀፍ የይሖዋ ሕዝቦች ጉባኤ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአል። በዘመናችን አንዳንድ ቦታቸውን የማይጠብቁ ሴቶች ባሎቻቸው ከሃዲዎች እንዲሆኑ ገፋፍተዋል። እንዲያውም በይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች ላይ ክስ እንዲመሠረት አድርገዋል።—ከ⁠ይሁዳ 5-8 ጋር አወዳድር።

  • “የሰይጣንን ጥልቅ ነገሮች” መጸየፍ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 10. (ሀ) ኤልዛቤልና ልጆችዋ ፍርድ የተቀበሉት ለምንድን ነው? (ለ) የኤልዛቤል ልጆች የሚሆኑ ሁሉ እንዴት ባለ አደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?

      10 ኢየሱስ ‘ስለዚህች ሴት ኤልዛቤል’ ሲናገር ቀጥሎ እንዲህ ብሎአል:- “ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፣ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።” (ራእይ 2:23) ኢየሱስ ኤልዛቤልና ልጆችዋ ንስሐ የሚገቡበት ጊዜ ሰጥቶአቸው ነበር። ይሁን እንጂ ከሴሰኝነት መንገዳቸው ፈቀቅ ለማለት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፍርዳቸውን መቀበል ይኖርባቸዋል። እዚህ ላይ በዘመናችን የሚኖሩትን ክርስቲያኖች በሙሉ የሚያሳስብ ኃይለኛ ማስጠንቀቂያ አለ። ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የመጽሐፍ ቅዱስን የራስነት መሠረታዊ ሥርዓት ወይም የሥነ ምግባር ሕግ በመጣስ ወይም በትዕቢተኛነት ቲኦክራቲካዊ ሥርዓቶችን በመቃወም የኤልዛቤልን ምሳሌ በመከተል ልጆችዋ ከሆኑ አደገኛ መንፈሳዊ በሽታ ይዞአቸዋል ማለት ነው። እውነት ነው፣ እንደዚህ ያለው ሰው በጉባኤው ውስጥ ያሉትን ሽማግሌዎች ጠርቶ እንዲጸልዩለት ቢጠይቃቸው “የእምነት ጸሎት ድውዩን ያድናል። ጌታም [“ይሖዋም፣” NW] ያስነሳዋል።” ይህ የሚሆነው ግን ከቀረበለት ጸሎት ጋር ተስማምቶ በትህትና ሲኖር ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ማንም ቢሆን የፈጸመውን ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ድርጊት በመሰወር ወይም በቅንዓት እንደሚያገለግል በማስመሰል አምላክን ወይም ክርስቶስን ለማታለል እችላለሁ ብሎ ማሰብ አይኖርበትም።—ያዕቆብ 5:14, 15

      11. የዘመናችን ጉባኤዎች ሕገወጥ የሆነ የሴቶች ተጽእኖ እንዳይኖር ነቅተው መጠበቅ የሚኖርባቸው ለምንድን ነው?

      11 በዘመናችን ያሉት አብዛኞቹ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ለዚህ አደገኛ ሁኔታ ንቁ መሆናቸው በጣም ያስደስታል። ሽማግሌዎች ቲኦክራቲካዊ ያልሆነ ዝንባሌ ወይም መጥፎ ሥነ ምግባር እንዳይስፋፋ ተጠንቅቀው ይጠባበቃሉ። በአደገኛ ጎዳና ላይ የሚገኙ ወንዶች ወይም ሴቶች ርቀው ከመሄዳቸው በፊት መንፈሳዊነታቸውን ገንብተው እንዲስተካከሉ ለመርዳት የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። (ገላትያ 5:16፤ 6:1) እነዚህ ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች እንደ ሴቶች ነፃነት እንቅስቃሴ የመሰለ ጠባብ ዓላማ ያለው የሴቶች ቡድን እንዳይፈጠር በፍቅርና በቆራጥነት ያግዳሉ። ከዚህም በላይ የይሖዋ ምሥክሮች በሚያዘጋጇቸው ጽሑፎች አማካኝነት ከወቅቱ ጋር የሚስማማ ትምህርት በየጊዜው ይሰጣል።a

      12. የዮሐንስ ክፍል በዘመናችን የኢዩን የመሰለ ቅንዓት ያሳየው በምን መንገድ ነው?

      12 ይሁን እንጂ ከባድ ኃጢአት ከተሠራ ይህን ኃጢአት የሠሩ ሰዎች በተለይም ኃጢአትን ልማዳቸው ያደረጉና ንስሐ ለመግባት የማይፈልጉ ከሆኑ መወገድ ይኖርባቸዋል። ኢዩ የኤልዛቤልን ግፊት ከእሥራኤል ምድር ፈጽሞ ለማጥፋት ያሳየውን ቅንዓት እናስታውሳለን። የዘመናችን የዮሐንስ ክፍልም በተመሳሳይ ተባባሪው ለሆነው ‘የኢዮናዳብ’ ክፍል ምሳሌ የሚሆንና ልቅ መሆንን ከሚፈቅዱት የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት ፈጽሞ የተለየ መሆኑን የሚያሳይ ጠንካራ እርምጃ ይወስዳል።—2 ነገሥት 9:22, 30-37፤ 10:12-17

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ