-
“የሰይጣንን ጥልቅ ነገሮች” መጸየፍራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
8. (ሀ) ኢየሱስ በትያጥሮን ስለነበረችው “ኤልዛቤል” ምን ውሳኔ አስተላልፎ ነበር? (ለ) በዘመናችን ተገቢ ያልሆነ የሴቶች ተጽዕኖ የታየው እንዴት ነው?
8 ኢየሱስ በመቀጠል በትያጥሮን ለነበሩት ሽማግሌዎች እንዲህ ይላቸዋል:- “ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም። እነሆ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፣ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ።” (ራእይ 2:21, 22) የመጀመሪያዋ ኤልዛቤል በአክዓብ ላይ እንደሰለጠነችና የአምላክ ፍርድ አስፈጻሚ የነበረውን ኢዩን እንደናቀች ሁሉ ይህም በትያጥሮን ጉባኤ የነበረው የሴቶች ተጽእኖ ባሎችንና ሽማግሌዎችን በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ ሞክሮ ነበር። በትያጥሮን ጉባኤ የነበሩትም ሽማግሌዎች ይህን ትህትና የጎደለውን የኤልዛቤል ተጽእኖ በቸልታ የተመለከቱት ይመስላል። ኢየሱስ እዚህ ላይ ለእነርሱም ሆነ በዘመናችን ላለው ምድር አቀፍ የይሖዋ ሕዝቦች ጉባኤ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአል። በዘመናችን አንዳንድ ቦታቸውን የማይጠብቁ ሴቶች ባሎቻቸው ከሃዲዎች እንዲሆኑ ገፋፍተዋል። እንዲያውም በይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች ላይ ክስ እንዲመሠረት አድርገዋል።—ከይሁዳ 5-8 ጋር አወዳድር።
-
-
“የሰይጣንን ጥልቅ ነገሮች” መጸየፍራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
10. (ሀ) ኤልዛቤልና ልጆችዋ ፍርድ የተቀበሉት ለምንድን ነው? (ለ) የኤልዛቤል ልጆች የሚሆኑ ሁሉ እንዴት ባለ አደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?
10 ኢየሱስ ‘ስለዚህች ሴት ኤልዛቤል’ ሲናገር ቀጥሎ እንዲህ ብሎአል:- “ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፣ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።” (ራእይ 2:23) ኢየሱስ ኤልዛቤልና ልጆችዋ ንስሐ የሚገቡበት ጊዜ ሰጥቶአቸው ነበር። ይሁን እንጂ ከሴሰኝነት መንገዳቸው ፈቀቅ ለማለት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ፍርዳቸውን መቀበል ይኖርባቸዋል። እዚህ ላይ በዘመናችን የሚኖሩትን ክርስቲያኖች በሙሉ የሚያሳስብ ኃይለኛ ማስጠንቀቂያ አለ። ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የመጽሐፍ ቅዱስን የራስነት መሠረታዊ ሥርዓት ወይም የሥነ ምግባር ሕግ በመጣስ ወይም በትዕቢተኛነት ቲኦክራቲካዊ ሥርዓቶችን በመቃወም የኤልዛቤልን ምሳሌ በመከተል ልጆችዋ ከሆኑ አደገኛ መንፈሳዊ በሽታ ይዞአቸዋል ማለት ነው። እውነት ነው፣ እንደዚህ ያለው ሰው በጉባኤው ውስጥ ያሉትን ሽማግሌዎች ጠርቶ እንዲጸልዩለት ቢጠይቃቸው “የእምነት ጸሎት ድውዩን ያድናል። ጌታም [“ይሖዋም፣” NW] ያስነሳዋል።” ይህ የሚሆነው ግን ከቀረበለት ጸሎት ጋር ተስማምቶ በትህትና ሲኖር ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ማንም ቢሆን የፈጸመውን ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ድርጊት በመሰወር ወይም በቅንዓት እንደሚያገለግል በማስመሰል አምላክን ወይም ክርስቶስን ለማታለል እችላለሁ ብሎ ማሰብ አይኖርበትም።—ያዕቆብ 5:14, 15
-
-
“የሰይጣንን ጥልቅ ነገሮች” መጸየፍራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
13. ለተሳሳተ የሴቶች ተጽእኖ የሚሸነፉ ሁሉ ምን ይሆናሉ?
13 የአምላክ ልጅ የይሖዋ መልእክተኛና ፈራጅ እንደመሆኑ መጠን ዘመናዊቷ ኤልዛቤል ማን መሆንዋን ለይቶ ማሳወቁና በበሽታ ተመትታ የአልጋ ቁራኛ እንድትሆን ማድረጉ ተገቢ ነው። በእርግጥም መንፈሳዊ በሽታዋ በጣም የበረታና ስር የሰደደ ነው። (ሚልክያስ 3:1, 5) ለዚህ ዓይነቱ የተሳሳተ የሴቶች ግፊት የተሸነፉ ሁሉ እንደ ሙታን ተቆጥረው ከክርስቲያን ጉባኤ የመወገድ ሐዘንና ታላቅ መከራ ይደርስባቸዋል። እነዚህ ሰዎች ንስሐ ገብተው ካልተመለሱና ጉባኤው እንደገና ካልተቀበላቸው ተቀስፈው ሥጋዊ ሞት ሳይሞቱ የሚቆዩት እጅግ ቢበዛ እስከ ታላቁ መከራ ብቻ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ከመሆኑ በፊት ሙሉ በሙሉ ከበደላቸው ተጸጽተው ንስሐ ቢገቡ እንደገና ሊስተካከሉ ይችላሉ።—ማቴዎስ 24:21, 22፤ 2 ቆሮንቶስ 7:10
-