የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢየሱስ የሚያበረታታ መልእክት ይዞ መጣ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 1. አሁን ዮሐንስ የጻፈው ለማን ነው? በአሁኑ ጊዜ እርሱ ስለጻፈው መልእክት አጥብቀው ማሰብ የሚኖርባቸው እነማን ናቸው?

      ቀጥሎ የሆነው ነገር ዛሬ ከአምላክ ሕዝቦች ጉባኤ ጋር የተባበሩትን ሁሉ ከልብ የሚነካ ነገር ነው። ከዚህ በታች ተከታታይ የሆኑ መልእክቶች ቀርበዋል። እነዚህ መልእክቶች “ዘመኑ” እየቀረበ በሄደ መጠን የተለየ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል። (ራእይ 1:3) እነዚህን መግለጫዎች ማስተዋላችን የዘላለም በረከት ያስገኝልናል። የተመዘገበው መልእክት እንዲህ ይላል:- “ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፣ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፣ . . . ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።”—ራእይ 1:4, 5ሀ

  • ኢየሱስ የሚያበረታታ መልእክት ይዞ መጣ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 3. (ሀ) ዮሐንስ በሰላምታው እንደገለጸው “ጸጋና [“የማይገባ ደግነትና፣” NW] ሰላም” የሚገኘው ከየት ነው? (ለ) ከዮሐንስ ሰላምታ ጋር የሚመሳሰለው የትኛው የሐዋርያው ጳውሎስ አነጋገር ነው?

      3 “ጸጋና [“የማይገባ ደግነትና፣” NW] ሰላም” በተለይ ከየት እንደሚገኙ ስናስተውል በጣም ተፈላጊ ነገሮች መሆናቸውን እንገነዘባለን። “ጸጋና ሰላም” የሚፈስሰው “የዘላለም ንጉሥ” ከሆነውና “ከዘላለም እስከ ዘላለም” ከሚኖረው ሉዓላዊ ገዥ ከይሖዋ ነው። (1 ጢሞቴዎስ 1:17፤ መዝሙር 90:2) እዚህ ላይ “ሰባቱ መናፍስት” ተጠቅሰዋል። ይህም ቃል የአምላክ አንቀሳቃሽ ኃይል ወይም መንፈስ ቅዱስ ትንቢቱን ለሚከታተሉት ሁሉ ማስተዋልና በረከት በሚያመጣበት ጊዜ በተሟላ ሁኔታ እንደሚሠራ ያመለክታል። በተጨማሪም ለኢየሱስ ክርስቶስ ቁልፍ ቦታ ተሰጥቶታል። ስለ እርሱም ዮሐንስ “ጸጋና እውነት” የተሞላ እንደሆነ ጽፎአል። (ዮሐንስ 1:14) ስለዚህ የዮሐንስ ሰላምታ ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ጉባኤ የጻፈውን ሁለተኛ መልእክቱን ሲደመድም “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ [“የማይገባ ደግነት፣” NW]፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን” በማለት ከተናገረው ጋር ተመሳሳይነት አለው። (2 ቆሮንቶስ 13:14) ይህ ቃል ዛሬ እውነትን ለምናፈቅር ሁሉ እንዲፈጸምልን ከልብ እንመኛለን።—መዝሙር 119:97

      “ታማኙ ምስክር”

      4. ዮሐንስ ኢየሱስ ክርስቶስን የገለጸው እንዴት ነው? ይህስ መግለጫ ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?

      4 ከይሖዋ ቀጥሎ በጽንፈ ዓለሙ ውስጥ ከሁሉ የበለጠ ታላቅ ግርማ ያለው አካል ኢየሱስ ነው። ዮሐንስም ይህን በመረዳት “የታመነው ምስክር፣ የሙታንም በኩር፣ የምድርም ነገሥታት ገዥ” ሲል ገልጾታል። (ራእይ 1:5ለ) በሰማያት እንዳለው ጨረቃ ለይሖዋ አምላክነት ታላቅ ምሥክር በመሆን በማይናወጥ ሁኔታ ተመሥርቶአል። (መዝሙር 89:37) መሥዋዕት ሆኖ እስከመሞት ድረስ ፍጹም አቋሙን ከጠበቀ በኋላ ከሰው ልጆች መካከል ከሙታን ተነስቶ የማይሞት መንፈሳዊ ሕይወት ለማግኘት የመጀመሪያው ሆነ። (ቆላስይስ 1:18) አሁን ደግሞ በይሖዋ ፊት ቀርቦ “በሰማይና በምድር ሁሉ ሥልጣን” ስለተሰጠው ከምድር ነገሥታት ሁሉ በላይ ከፍ ተደርጎአል። (ማቴዎስ 28:18፤ መዝሙር 89:27፤ 1 ጢሞቴዎስ 6:15) በ1914 የምድር አሕዛብን ሁሉ እንዲገዛ ንጉሥ ሆኖ ተሹሞአል።—መዝሙር 2:6-9

      5. (ሀ) ዮሐንስ ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን አድናቆት የገለጸው እንዴት ነው? (ለ) ኢየሱስ ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ የሚጠቀሙት እነማን ናቸው? ቅቡዓን ክርስቲያኖችስ ልዩ በሆኑ በረከቶች የተካፈሉት እንዴት ነው?

      5 ዮሐንስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን አድናቆት መግለጹን በመቀጠል የሚከተሉትን ሞቅ ያሉ ቃላት ተናግሯል:- “ለወደደን፣ ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፣ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።” (ራእይ 1:5ሐ, 6) ኢየሱስ በእርሱ የሚያምነው የሰው ልጆች ዓለም በሙሉ ፍጹም ሕይወት መልሶ ለማግኘት እንዲችል ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን መሥዋዕት አደረገ። አንተም ውድ አንባቢ፣ ከዚህ ክፍል ለመሆን ትችላለህ! (ዮሐንስ 3:16) ይሁን እንጂ የኢየሱስ መሥዋዕታዊ ሞት እንደ ዮሐንስ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ለሚሆኑት ሁሉ ልዩ በረከት ለማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ከፍቶላቸዋል። እነዚህ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ምክንያት ጻድቃን ሆናችኋል ተብሎ ተነግሮላቸዋል። የታናሹ መንጋ አባሎች ልክ እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ የመኖር ዕድላቸውን በመተው በአምላክ መንፈስ ቅዱስ ተወልደዋል። ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋርም በመንግሥቱ ነገሥታትና ካህናት ሆነው ለማገልገል ከሙታን እንደሚነሱ ተስፋ ያደርጋሉ። (ሉቃስ 12:32፤ ሮሜ 8:18፤ 1 ጴጥሮስ 2:5፤ ራእይ 20:6) ይህ እንዴት ያለ ታላቅ መብት ነው! ዮሐንስ በጋለ ስሜት ክብርና ኃይል የኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ማረጋገጡ አያስደንቅም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ