የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስምህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኛልን?
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 3. (ሀ) ‘የሰርዴስ ጉባኤ መልአክ’ ኢየሱስ “ሰባቱ ከዋክብት” ያሉት መሆኑን በጥሞና መገንዘብ የነበረበት ለምንድን ነው? (ለ) ኢየሱስ በሰርዴስ ለነበረው ጉባኤ ምን ጠንካራ ምክር ሰጥቶአል?

      3 በተጨማሪም ኢየሱስ ‘የሰርዴስን ጉባኤ መልአክ’ “ሰባቱ ከዋክብት” ያሉት መሆኑን አስገንዝቦታል። እነዚህን የጉባኤ ሽማግሌዎች በቀኝ እጁ ውስጥ ስለያዛቸው በእረኝነት ሥራቸው ሊመራቸውና ሊቆጣጠራቸው ሥልጣን አለው ማለት ነው። የመንጋውን መልክ ለማወቅ ልባዊ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። (ምሳሌ 27:23) ስለዚህ የሚቀጥለውን የኢየሱስ ቃል ልብ ብለው ቢያዳምጡ ይበጃቸዋል። “ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፣ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና፣ እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፣ ጠብቀውም ንስሐም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።”—ራእይ 3:2, 3

      4. ጴጥሮስ የተናገራቸው ቃላት የሰርዴስ ጉባኤ ‘የቀሩትን ነገሮች እንዲያጸና’ የሚረዳው እንዴት ነው?

      4 በሰርዴስ የነበሩት ሽማግሌዎች መጀመሪያ እውነትን ባወቁበት ጊዜ የተሰማቸውን ደስታና በዚያ ጊዜ ያገኙትን በረከት ማሰብ ያስፈልጋቸው ነበር። አሁን ግን በመንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸው ረገድ ሙታን ሆነዋል። የጉባኤ መብራታቸው የእምነት ሥራ ስለጎደለው ብልጭ እልም ይል ነበር። ከዓመታት በፊት ሐዋርያው ጴጥሮስ በእሥያ ለነበሩት ጉባኤዎች (ሰርዴስንም ሳይጨምር አይቀርም) ክርስቲያኖች ለተቀበሉት (በዮሐንስ ራእይ ውስጥ በሰባት መናፍስት በተመሰለው) ‘ከሰማይ የተላከ መንፈስ ቅዱስ’ ለታወጀው ታላቅ የምሥራች ያላቸውን አድናቆት እንዲያሳድጉ መክሮ ነበር። በተጨማሪም ጴጥሮስ እነዚህ የእስያ ክርስቲያኖች ‘ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራቸውን የእርሱን በጎነት እንዲነግሩ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ ለርስቱ የተለየ ወገን’ እንዲሆኑ አሳስቦአቸው ነበር። (1 ጴጥሮስ 1:12, 25፤ 2:9) የሰርዴስ ጉባኤ በእነዚህ መንፈሳዊ እውነቶች ላይ ቢያሰላስል ንስሐ ሊገባና “የቀሩትን ነገሮች” ሊያጸና ይችላል።—ከ⁠2 ጴጥሮስ 3:9 ጋር አወዳድር።

      5. (ሀ) በሰርዴስ የነበሩት ክርስቲያኖች የአድናቆት ስሜት ምን ሆኖ ነበር? (ለ) የሰርዴስ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ምክር ካልተቀበሉ ምን ይደርስባቸዋል?

      5 በወቅቱ ለእውነት ያላቸው ፍቅርና አድናቆት ሊጠፋ እንደተቃረበ እሳት ሆኖ ነበር። ጥቂት ፍሞች ብቻ ቀርተው ነበር። ኢየሱስ ቸልተኝነታቸው ካስከተለባቸው ኃጢአት ንስሐ በመግባትና እንደገና መንፈሳዊ ሕይወት ያለው ጉባኤ በመሆን እነዚህን የቀሩትን ፍሞች እንዲቆሰቁሱና እንዲያራግቡ አበረታታቸው። (ከ⁠2 ጢሞቴዎስ 1:6, 7 ጋር አወዳድር።) አለዚያ ግን ኢየሱስ ፍርድ ለመስጠት ባልተጠበቀ ሁኔታ “እንደ ሌባ” በሚመጣበት ጊዜ በሰርዴስ የነበረው ጉባኤ ዝግጁ ሆኖ አይገኝም።—ማቴዎስ 24:43, 44

  • ስምህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኛልን?
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 7. ዛሬ ክርስቲያኖች ነቅተው መጠባበቅ የሚኖርባቸው ለምንድን ነው?

      7 ለማንኛውም ክርስቲያን ንቁ ሆኖ የመጠበቅ አስፈላጊነት በጌታ ቀን መጀመሪያ ላይ አላበቃም። ኢየሱስ “ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድን ነው” በማለት ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ በተናገረው ታላቅ ትንቢት የሚከተለውን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአል። “ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት . . . የሚያውቅ የለም። ጊዜው መቼ እንደሆነ አታውቁምና ተጠንቀቁ፣ ትጉ፣ ጸልዩም። ለእናንተም የምነግራችሁን ለሁሉ እላለሁ፣ ትጉ።” (ማርቆስ 13:4, 32, 33, 37) አዎ፣ ሁላችንም ከቅቡዓን ክፍልም ሆንን ከእጅግ ብዙ ሰዎች ክፍል እስከዚያች ሰዓት ድረስ ንቁዎች ሆነን ለመኖርና መንፈሳዊ እንቅልፍ እንዳያሸልበን ለመከላከል ነቅተን መጠባበቅ ይኖርብናል። የይሖዋ ቀን ‘እንደ ሌባ በሌሊት ሲመጣ’ ጥሩ ፍርድ እንዲፈረድልን ነቅተን እንጠባበቅ።—1 ተሰሎንቄ 5:2, 3፤ ሉቃስ 21:34-36፤ ራእይ 7:9

      8. በዘመናችን የዮሐንስ ክፍል የአምላክ ሕዝቦች በመንፈሳዊ ሕያው ሆነው እንዲኖሩ የቀሰቀሰው እንዴት ነው?

      8 በዛሬው ዘመን ያለው የዮሐንስ ክፍል የአምላክ ሕዝቦችን በመንፈሳዊ ሕያው ሆነው እንዲጠባበቁ መቀስቀስ አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝቦአል። ለዚህም ሲባል በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ብዙ ታላላቅ ስብሰባዎች ይደረጋሉ። በቅርብ ዓመት በተደረጉት 2,981 የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በጠቅላላው 10,953,744 ሰዎች ሲገኙ 122,701 አዳዲስ አማኞች ተጠምቀዋል። የዮሐንስ ክፍል ከመቶ ለሚበልጡ ዓመታት መጠበቂያ ግንብ የተባለውን መጽሔት የይሖዋን ስምና ዓላማ ለማወጅ ሲጠቀምበት ቆይቶአል። በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ዓመታት ከባድ ስደት በተነሳ ጊዜ በመጠበቂያ ግንብ ላይ “ደፋሮች የተባረኩ ናቸው” (1919)፣ “ለሥራ የመነሳት ጥሪ” (1925)፣ “የስደት መሸነፍ” (1942) እንደሚሉት ያሉትን ርዕሰ ትምህርቶች በማውጣት የይሖዋ ምሥክሮችን ቅንዓት በአዲስ ሁኔታ አነሳስተዋል።

      9. (ሀ) ክርስቲያኖች ሁሉ ራሳቸውን ምን ብለው መጠየቅ ይኖርባቸዋል? (ለ) መጠበቂያ ግንብ እንዴት ያለ ማበረታቻ ሰጥቶ ነበር?

      9 በዛሬዎቹ ጉባኤዎች የሚገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ በሰርዴስ ጉባኤ እንደነበሩት ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ራሳቸውን መመርመር ያስፈልጋቸዋል። ሁላችንም ራሳችንን ‘ሥራዬ በአምላክ ዘንድ ፍጹም ሆኖ ይገኛልን?’ ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። በሌሎች ላይ ሳንፈርድ በየግላችን ራስን መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ እየኮተኮትን አምላክን በሙሉ ነፍሳችን ለማገልገል እንጥራለንን? በዚህም ረገድ መጠበቂያ ግንብ “ራሳችሁን ፈትኑ” እና “ከእንግዲህ ለራሳችን አንኖርም” እንደሚሉት ያሉትን ትምህርቶች በማውጣት ማበረታቻ ሰጥቶአል።a እንደነዚህ ባሉት ቅዱስ ጽሑፋዊ እርዳታዎች በመጠቀም በይሖዋ ፊት ፍጹም አቋማችንን ጠብቀን በትህትናና በጸሎተኝነት መንፈስ ለመመላለስ በምንጥርበት ጊዜ ውስጣዊ ልቦናችንን ዘወትር እንመርምር።—መዝሙር 26:1-3፤ 139:23, 24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ