የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስምህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኛልን?
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 3. (ሀ) ‘የሰርዴስ ጉባኤ መልአክ’ ኢየሱስ “ሰባቱ ከዋክብት” ያሉት መሆኑን በጥሞና መገንዘብ የነበረበት ለምንድን ነው? (ለ) ኢየሱስ በሰርዴስ ለነበረው ጉባኤ ምን ጠንካራ ምክር ሰጥቶአል?

      3 በተጨማሪም ኢየሱስ ‘የሰርዴስን ጉባኤ መልአክ’ “ሰባቱ ከዋክብት” ያሉት መሆኑን አስገንዝቦታል። እነዚህን የጉባኤ ሽማግሌዎች በቀኝ እጁ ውስጥ ስለያዛቸው በእረኝነት ሥራቸው ሊመራቸውና ሊቆጣጠራቸው ሥልጣን አለው ማለት ነው። የመንጋውን መልክ ለማወቅ ልባዊ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። (ምሳሌ 27:23) ስለዚህ የሚቀጥለውን የኢየሱስ ቃል ልብ ብለው ቢያዳምጡ ይበጃቸዋል። “ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፣ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና፣ እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፣ ጠብቀውም ንስሐም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።”—ራእይ 3:2, 3

  • ስምህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኛልን?
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 5. (ሀ) በሰርዴስ የነበሩት ክርስቲያኖች የአድናቆት ስሜት ምን ሆኖ ነበር? (ለ) የሰርዴስ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ምክር ካልተቀበሉ ምን ይደርስባቸዋል?

      5 በወቅቱ ለእውነት ያላቸው ፍቅርና አድናቆት ሊጠፋ እንደተቃረበ እሳት ሆኖ ነበር። ጥቂት ፍሞች ብቻ ቀርተው ነበር። ኢየሱስ ቸልተኝነታቸው ካስከተለባቸው ኃጢአት ንስሐ በመግባትና እንደገና መንፈሳዊ ሕይወት ያለው ጉባኤ በመሆን እነዚህን የቀሩትን ፍሞች እንዲቆሰቁሱና እንዲያራግቡ አበረታታቸው። (ከ⁠2 ጢሞቴዎስ 1:6, 7 ጋር አወዳድር።) አለዚያ ግን ኢየሱስ ፍርድ ለመስጠት ባልተጠበቀ ሁኔታ “እንደ ሌባ” በሚመጣበት ጊዜ በሰርዴስ የነበረው ጉባኤ ዝግጁ ሆኖ አይገኝም።—ማቴዎስ 24:43, 44

      “እንደ ሌባ” ሆኖ መምጣት

      6. ኢየሱስ በ1918 “እንደ ሌባ” በድንገት የመጣው እንዴት ነው? ተከታዮቹ ነን ይሉ በነበሩ ሰዎች መካከል እንዴት ያለ ሁኔታ አገኘ?

      6 ኢየሱስ “እንደ ሌባ” እንደሚመጣ የሰጠው ማስጠንቀቂያ አስፈላጊነት እስከ ዘመናችን ድረስ ቆይቶአል። በተለይ በጌታ ቀን ውስጥ ለሚገኙት ክርስቲያኖች ልዩ ትርጉም ነበረው። ከ1914 ብዙም ሳይቆይ የሚከተለው የሚልክያስ ትንቢት ተፈጸመ። “እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወድዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ እነሆ ይመጣል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW]።” (ሚልክያስ 3:1፤ ራእይ 1:10) ኢየሱስ ‘የቃል ኪዳኑ መልእክተኛ’ እንደመሆኑ መጠን ተከታዮቹ ነን የሚሉትን ሊቆጣጠርና ሊፈርድ መጣ። (1 ጴጥሮስ 4:17) በ1918 ሕዝበ ክርስትና በመጀመሪያው ዓለም ጦርነት ደም በማፋሰስ ተግባር ሙሉ በሙሉ ተውጣ ስለነበረ በመንፈሳዊ አነጋገር ፈጽሞ በድን ሆና ነበር። ከጦርነቱ በፊት በቅንዓት ይሰብኩ የነበሩት እውነተኛ ክርስቲያኖች እንኳን መንፈሳዊ ሰመመን ይዞአቸው ነበር። ከግንባር ቀደም ሽማግሌዎቻቸው አንዳንዶቹ በእስር ላይ ይገኙ ስለነበረ የስብከቱ ሥራ ቆሞ ነበር። በሚቀጥለው ዓመት የይሖዋ መንፈስ እነዚህን ክርስቲያኖች ቀስቅሶ ባስነሳቸው ጊዜ ዝግጁ ሆነው የተነሱት ሁሉም ክርስቲያኖች አልነበሩም። አንዳንዶቹ በኢየሱስ ምሳሌ እንደተጠቀሱት ሞኝ ቆነጃጅት ይሖዋን የማገልገልን መብት ለመቀበል መንፈሳዊ ዝግጅት አልነበራቸውም። ይሁን እንጂ እንደ ልባሞቹ ቆነጃጅት “ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ” በማለት ኢየሱስ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ጠብቀው የተገኙ ብዙ ክርስቲያኖች ነበሩ።—ማቴዎስ 25:1-13

      7. ዛሬ ክርስቲያኖች ነቅተው መጠባበቅ የሚኖርባቸው ለምንድን ነው?

      7 ለማንኛውም ክርስቲያን ንቁ ሆኖ የመጠበቅ አስፈላጊነት በጌታ ቀን መጀመሪያ ላይ አላበቃም። ኢየሱስ “ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድን ነው” በማለት ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ በተናገረው ታላቅ ትንቢት የሚከተለውን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶአል። “ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት . . . የሚያውቅ የለም። ጊዜው መቼ እንደሆነ አታውቁምና ተጠንቀቁ፣ ትጉ፣ ጸልዩም። ለእናንተም የምነግራችሁን ለሁሉ እላለሁ፣ ትጉ።” (ማርቆስ 13:4, 32, 33, 37) አዎ፣ ሁላችንም ከቅቡዓን ክፍልም ሆንን ከእጅግ ብዙ ሰዎች ክፍል እስከዚያች ሰዓት ድረስ ንቁዎች ሆነን ለመኖርና መንፈሳዊ እንቅልፍ እንዳያሸልበን ለመከላከል ነቅተን መጠባበቅ ይኖርብናል። የይሖዋ ቀን ‘እንደ ሌባ በሌሊት ሲመጣ’ ጥሩ ፍርድ እንዲፈረድልን ነቅተን እንጠባበቅ።—1 ተሰሎንቄ 5:2, 3፤ ሉቃስ 21:34-36፤ ራእይ 7:9

      8. በዘመናችን የዮሐንስ ክፍል የአምላክ ሕዝቦች በመንፈሳዊ ሕያው ሆነው እንዲኖሩ የቀሰቀሰው እንዴት ነው?

      8 በዛሬው ዘመን ያለው የዮሐንስ ክፍል የአምላክ ሕዝቦችን በመንፈሳዊ ሕያው ሆነው እንዲጠባበቁ መቀስቀስ አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝቦአል። ለዚህም ሲባል በየዓመቱ በዓለም ዙሪያ ብዙ ታላላቅ ስብሰባዎች ይደረጋሉ። በቅርብ ዓመት በተደረጉት 2,981 የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በጠቅላላው 10,953,744 ሰዎች ሲገኙ 122,701 አዳዲስ አማኞች ተጠምቀዋል። የዮሐንስ ክፍል ከመቶ ለሚበልጡ ዓመታት መጠበቂያ ግንብ የተባለውን መጽሔት የይሖዋን ስምና ዓላማ ለማወጅ ሲጠቀምበት ቆይቶአል። በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ዓመታት ከባድ ስደት በተነሳ ጊዜ በመጠበቂያ ግንብ ላይ “ደፋሮች የተባረኩ ናቸው” (1919)፣ “ለሥራ የመነሳት ጥሪ” (1925)፣ “የስደት መሸነፍ” (1942) እንደሚሉት ያሉትን ርዕሰ ትምህርቶች በማውጣት የይሖዋ ምሥክሮችን ቅንዓት በአዲስ ሁኔታ አነሳስተዋል።

      9. (ሀ) ክርስቲያኖች ሁሉ ራሳቸውን ምን ብለው መጠየቅ ይኖርባቸዋል? (ለ) መጠበቂያ ግንብ እንዴት ያለ ማበረታቻ ሰጥቶ ነበር?

      9 በዛሬዎቹ ጉባኤዎች የሚገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ በሰርዴስ ጉባኤ እንደነበሩት ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ራሳቸውን መመርመር ያስፈልጋቸዋል። ሁላችንም ራሳችንን ‘ሥራዬ በአምላክ ዘንድ ፍጹም ሆኖ ይገኛልን?’ ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። በሌሎች ላይ ሳንፈርድ በየግላችን ራስን መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ እየኮተኮትን አምላክን በሙሉ ነፍሳችን ለማገልገል እንጥራለንን? በዚህም ረገድ መጠበቂያ ግንብ “ራሳችሁን ፈትኑ” እና “ከእንግዲህ ለራሳችን አንኖርም” እንደሚሉት ያሉትን ትምህርቶች በማውጣት ማበረታቻ ሰጥቶአል።a እንደነዚህ ባሉት ቅዱስ ጽሑፋዊ እርዳታዎች በመጠቀም በይሖዋ ፊት ፍጹም አቋማችንን ጠብቀን በትህትናና በጸሎተኝነት መንፈስ ለመመላለስ በምንጥርበት ጊዜ ውስጣዊ ልቦናችንን ዘወትር እንመርምር።—መዝሙር 26:1-3፤ 139:23, 24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ