-
ስምህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኛልን?ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
10. ኢየሱስ በሰርዴስ ጉባኤ ውስጥ ምን አበረታች ሁኔታ ተመልክቶ ነበር? ይህስ እኛን እንዴት ሊነካን ይገባል?
10 ኢየሱስ ቀጥሎ ለሰርዴስ ጉባኤ የተናገረው ቃል በጣም የሚያበረታታ ነው። እንዲህ አለ:- “ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ስሞች ከአንተ ጋር አሉ፣ የተገባቸውም ስለሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ። ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጎናጸፋል፣ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፣ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ።” (ራእይ 3:4, 5) እነዚህ ቃላት የሚያነቃቁንና በታማኝነት ለመጽናት ያደረግነውን ውሣኔ የሚያጠነክሩልን አይደሉምን? አንድ ጉባኤ በአጠቃላይ በሽማግሌዎቹ አካል ቸልተኝነት ምክንያት ከባድ መንፈሳዊ እንቅልፍ ሊወስደው ይችላል። ይሁን እንጂ በጉባኤው ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦች ክርስቲያናዊ መለያቸው እንዳይቆሽሽባቸውና እንዳይበላሽባቸው በድፍረት ጥረት እያደረጉ በይሖዋ ዘንድ መልካም ስም እንዲኖራቸው ለማድረግ ይችላሉ።—ምሳሌ 22:1
-
-
ስምህ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ይገኛልን?ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
13. ‘መጎናጸፊያቸውን ያላረከሱ’ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ምን ዓይነት በረከት ተዘጋጅቶላቸዋል?
13 እስከ መጨረሻው ጸንተው የተገኙትና ክርስቲያናዊ መታወቂያቸውን ያልጣሉት የሰርዴስ ክርስቲያኖች አስደናቂ ተስፋ መጨበጣቸው ይረጋገጣል። የኢየሱስ መሲሐዊት መንግሥት በ1914 ከተቋቋመች በኋላ መንፈሳዊ ሕይወት አግኝተው ከሙታን ተነስተዋል። ድል አድራጊዎች በመሆናቸውም ጉድለትና እንከን ለሌለበት የጽድቅ አቋማቸው ምሳሌ የሚሆን ነጭ መጎናጸፊያ ለብሰዋል። ወደ ሕይወት በሚወስደው ጠባብ መንገድ ሲመላለሱ ስለቆዩ ዘላለማዊ ሽልማት ይቀበላሉ።—ማቴዎስ 7:14፤ በተጨማሪም ራእይ 6:9-11 ተመልከት።
በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ለዘላለም መቆየት
14. “የሕይወት መጽሐፍ” ምንድን ነው? በዚያስ የተጻፉት የእነማን ስሞች ናቸው?
14 “የሕይወት መጽሐፍ” ምንድን ነው? በዚህስ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ የሚኖረው የእነማን ስም ነው? የሕይወት መጽሐፍ ወይም ጥቅልል የዘላለም ሕይወት ሽልማት ለማግኘት የተገባቸው ሆነው የተገኙ ሰዎች የሚጻፉበት የይሖዋ አገልጋዮች መዝገብ ነው። (ሚልክያስ 3:16) በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የቅቡዓን ክርስቲያኖች ስም በተለየ ሁኔታ ተጠቅሶአል። ይሁን እንጂ በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት የሚያገኙ ሰዎችም ስም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ይመዘገባል። ከዚህም በላይ አንዳንድ ስሞች ከዚህ መዝገብ ሊሰረዙ ይችላሉ። (ዘጸአት 32:32, 33) ሆኖም እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግበው የሚቆዩት የዮሐንስ ክፍል አባሎች በሰማይ ሞት የማይደፍረው የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል። (ራእይ 2:10) ኢየሱስ በአባቱና በመላእክቱ ፊት የሚመሰክርላቸው ስሞች እነዚህ ናቸው። ይህ የታማኝነታቸው ዋጋ እንዴት ያለ አስደናቂ ሽልማት ይሆናል!
15. የእጅግ ብዙ ሰዎች አባሎች ስሞቻቸውን በማይፋቅ ሁኔታ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የሚያስጽፉት እንዴት ነው?
15 በተጨማሪም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበላቸው እጅግ ብዙ ሰዎች ታላቁን መከራ በሕይወት ይሻገራሉ። በኢየሱስ የሺህ ዓመት ግዛት ዘመን በሙሉና ከዚያ በኋላ በሚመጣው ወሳኝ ፈተና እምነታቸውን ጠብቀው በመኖር በገነቲቱ ምድር የዘላለም ሕይወት የማግኘት ሽልማት ይቀበላሉ። (ዳንኤል 12:1፤ ራእይ 7:9, 14፤ 20:15፤ 21:4) ከዚያ በኋላ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ በማይፋቅ ሁኔታ ለዘላለም ይመዘገባል። የተዘጋጀው ሽልማት እንዴት ያለ እንደሆነ ካወቅህ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የቀረበውን የሚከተለውን የኢየሱስ ተደጋጋሚ ጥሪ ለመቀበል በግለት አትነሳሳምን? “መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።”—ራእይ 3:6
-